የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌደሬሽን 44ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ትናንት ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም በቫይብስ ሆቴል የ2018 ዓ.ም መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።
ፌደሬሽኑ በ2018 ዓ.ም የስራ ክንውን ያቀዳቸውን የውድድር የትምህርትና ስልጠና ተግባራትን በአግባቡ መሳካት የቻለ ሲሆን በስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራ ጃንሜዳን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ጋር በመሆን ለውድድርና ስልጠና አመች እንዲሆን አድርጓል።
በሌላ በኩል ከሲዳማ ክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን ጋር የልምድ ልውውጥ በማድረግ ጠቃሚ መረጃወችንና ተሞክሮዎችን ተለዋውጠዋል።
ለ2019 ዓ.ም የበጀት እቅድ ከባለፈው ውጤታማ የሆኑ ስራዎችን የበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለፀው ፌደሬሽኑ በአሁኑ ሰዓት የሀገራችን አትሌቲክ አደጋ ሆኖ የተጋረጠውን የዶፒንግ ጉዳይ ለማስቆም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር አበክረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
በጠቅላላ ጉባኤው በአመቱ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ተቋማትና አካላት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
መረጃው የአዲስአበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው።
2November 15, 2026 1.2K

