የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) መውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ ተከበረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 19 /2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 12/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
1 ሺህ 5 መቶ 1ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
በክብረ በዓሉ ላይ የፌዴራልና የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ዒማሞች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎ ተገኝተዋል ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን በክብረ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር የመውሊድ በዓልን ማከበር የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ ከማስታወስ ባለፈ አስተምህሯቸውንና ሱናቸውን በዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ መተግበር መሆኑን ገልጸዋል።
ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን በኢስላም ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን የመመካከር (ሹራ) እሴት በመጥቀስ ምክክር በቤተሰብ፣ በንግድና በማህበራዊ ህይወት አዎንታዊ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።
በሀገር ደረጃ የተካሄደው ምክክርም ሊበረታታ የሚገባው መልካም ጅምር መሆኑን የገለጹት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንቱ የምክክሩ ውጤቱ ለሀገርና ለህዝብ የሚበጅ እንዲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ዱዓ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሙሀመድ ሸሪፍ ሐሰን በበኩላቸው ሕዝበ ሙስሊሙ የነብዩ ሙሀመድን ፈለግ በመከተል ብቻ መውሊድን ሊያከብር ይገባል ብለዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ በከተማዋ እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ሥራዎች የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም ሸይኽ ሙሀመድ ሸሪፍ አስገንዝበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የነቢዩን ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) መልካም አርአያነት የሚያስታውሱ መንዙማዎች፣ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች የቀረቡ ሲሆን ለ6 ሺህ አቅመ ደካማ ወገኖችም የምግብ ማብላት መርሀ ግብር ተከናውኗል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት

August 25, 2026 1.4K 1