በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው ልዑክ ተፈጥሯዊውን የሶፍ ዑመር ዋሻ ጎበኘ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 22 /2018 ዓ.ል| ረቢዕ አል አወል 15/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ባሌ ሮቤ|
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው ልዑክ በታዋቂው መንፈሳዊ አባት ሸይኽ ሱፊ ዑመር አሕመድ ስም የሚጠራውንና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በጻፉት የመደመር ትውልድ መፅሀፍ ሽያጭ የለማውን ሶፍ ዑመር ዋሻ ጎበኘ።
ታሪካዊውና ተፈጥሯዊው የቱሪዝም መዳረሻ ሶፍ ዑመር ዋሻ ለሀገር እና ለህዝብ እየሰጠ ያለውን ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ጥቅም ለማሳደግ ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች ተሰርተዋል።
ሶፍ ዑመር ዋሻ ተፈጥሯውዊ እና ባህላዊ እሴቱ ተጠብቆ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች ምቹ እንዲሆን የተሰሩ ስራዎች የአካባቢውን የቱሪዝም ፍሰት ማሳደግ እንደቻሉ በጉብኝቱ ተመላክቷል።
በጉብኝቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ ምክትል ፕሬዝደንቶች ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ እና ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ፣ የአዲስ አበባ ከተማ እና የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ የስራ አስፈፃሚዎች፣ ዱዓቶች፣ የወጣት ካውንስል አመራሮች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተሳትፈዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
