ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
"ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን"
"ሁላችንም የአላህ ነን፤ ወደ እርሱም ተመላሾች ነን።"
በሀገረ አሜሪካ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን ያሰባሰበው የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን መሥራችና ለአርባ ዓመታት በመሪነት ያገለገሉት ሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ወደ አኺራ ተሻግረዋል።
ሐጂ ነጂብ ከፈርስት ሂጅራ መሥራችነት ባሻገር ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መብት መከበር በተለያዩ መልኩ ታግለዋል፤ ከቅድመ ድምጻችን ይሰማ ትግል ወቅት ጀምሮ የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎች በድፍረት ለመንግስት ግልጽ አድርገዋል።
የድምጻችን ይሰማ የመብት ማስከበር ትግል 2004 ላይ ሲጀመርም በሚዲያዎችና በሰላማዊ ሰልፎች ላይ በመገኘት የህዝበ ሙስሊሙን የመብት ጥያቄዎች ትክክኛነት አስረድተዋል። የመንግሥትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳና ስም ማጥፋት በማክሸፍም ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል።
የሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ሰላተል ጀናዛ በኒውሃምፕሻየር MCC መስጂድ ኦገስት 30/2016 በ1:30 PM የሚሰገድ ሲሆን ስርዓተ ቀብራቸው ደግሞ በአል ፊርደውስ መታሰቢያ ጋርደን ይፈጸማል።
ቤተሰቦቹ በፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ታዕዚያ የሚቀመጡ ሲሆን ሐጂ ነጂብ ሙሐመድ የአራት ልጆች አባትና የአምስት የልጅ ልጆች አያት ነበሩ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ህልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ አሏህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ለሟቹ ምሕረቱን ለግሶ ማረፊያቸውን ጀነት እንዲያደርግላቸው እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንዲሰጥ ይመኛል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
ነሀሴ 24/2018 ዓ.ል
ረቢዑል አወል 17/1448 ዓ.ሒ
