Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council: post #7051 — TG.ME

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ለባሌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የቢሮ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 23/2018 ዓ.ል| ረቢዕ አል አወል 16/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ባሌ ሮቤ|

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የባሌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለሚገነባው ባለ አምስት ወለል ሕንፃ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።

​በ1 ሺህ 7 መቶ 50 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት ላይ የሚያርፈው ይህ ዘመናዊ ሕንፃ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ለምክር ቤቱ ቢሮዎች እንዲሁም ለተለያዩ ተያያዥ አገልግሎቶች የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

​የህንጻ ግንባታው የዞኑ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለአገልግሎት አሰጣጡ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና ተቋማዊ አቅሙን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚያግዝ ተመላክቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ መጅሊስ ስራ አስፈጻሚ አባላትና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1