ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ ከህዝበ ሙስሊሙ እውቅናና ሽልማት ተበረከተለት።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 25/2018 ዓ.ል| ረቢዕ አል አወል 18/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ|
በሙስሊሞች መብት መከበር ዙሪያ ትኩረት አድርጎ ለበርካታ ዓመታት እየሰራ የሚገኘው ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ ለህዝበ ሙስሊሙ መብት መከበር ላበረከተው እና እያበረከተ ላለው ጉልህ አስተዋጽኦ ከህዝበ ሙስሊሙ እውቅናና ሽልማት ተበረከተለት።
ደረሳው ሰዒድ በሚል ስያሜ በሚሰራቸው ኢስላማዊ የኪነ ጥበብ ስራዎቹ የሚታወቀው ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ አሁን ላይ ሀሩን ሚዲያ በሚል ስያሜ በመሰረተው የሚዲያ ተቋሙ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሙስሊሞች መብት እንዲከበር እየሰራ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ሳፋየር አዲስ በተካሄደው የዕውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ላይ ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ የምስክር ወረቀት፣ የዋንጫ እና ልዩ ልዩ ስጦታዎች ተበርክተውለታል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የሚዲያን ሃያልነት እና ህዝበ ሙስሊሙ በዘርፉ ያለው ክፍተት የተገለጹ ሲሆን ለህዝበ ሙስሉሙ መብት መከበር እየተንቀሳቀሱ ያሉበእንደ ሃሩን ሚዲያ ያሉ ተቋማት እንዲጠናከሩ ሁሉም ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ተላልፏል።
በበጎ ፈቃደኛ ሙስሊሞች አስተባባሪነት እውቅና የተበረከተለት አብዱረሂም አህመድ የተሰጠው እውቅና በሚዲያ ዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።
በእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ መሻይሆች፣ ዱዓቶች፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች፣ የበጎ አድራጎት ተቋማት አመራሮችና የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የስራ ባልደረባዎቹ ተገኝተዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
