Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council: post #7056 — TG.ME

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ከክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

"እኛ የአላህ ነን፤ ወደ እርሱም ተመላሾች ነን።" ( አል-በቀራህ፡ 156)

​የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን መስራች አባል እና አመራር የነበሩት የተከበሩ ሀጂ ነጅብ ሙሀመድ ወደ አኺራ በመሻገራቸው የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ።

​ሀጂ ነጅብ ሙሀመድ ህይወታቸውን ሙሉ ለእስልምና እና ለህዝበ ሙስሊሙ ሲታገሉ ያሳለፉ፣ በሰብዓዊ እና በማህበረሰባዊ የልማት ስራዎች ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩ ታላቅ ሰው ነበሩ።

ሀጂ ነጅብ ሙሀመድ በፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን መስራችነታቸው እና አመራርነታቸው የኢስላማዊ እሴቶችን ለማስፋፋት፣ የታሪክ እና የቅርስ ጥበቃን ለማሻሻል እንዲሁም የህዝበ ሙስሊሙም አንድነት ለማጠናከር ሰርተዋል። ይህ በጎ ተግባራቸው በታሪክ እና በምእመናን ልብ ውስጥ ሲታወስ የሚኖር ነው።

​ለሟቹ ወንድማችን አላህ (ሱ.ወ) ሰፊ እዝነቱን እና ምህረቱን ለግሶ ጀነተል ፊርደውስን እንዲያጎናጽፋቸው እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው አላህ መፅናናትን እና ሰብርን እንዲሰጥ እየተመኘሁ ህዝበ ሙስሊሙ በየመስጂዶቹ ሶላተል ገይብ (የሩቅ ሶላት) እንዲሰግድላቸው ጥሪዬን አቀርባለሁ።

​የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት