በታላቁ አንዋር መስጂድ "ፍትሃዊው ነቢይ" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 17/2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 10 /1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ውልደት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በታላቁ አንዋር መስጂድ ተካሄደ።
ፓናል ውይይቱን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣት ጀምዓ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን የውይይት መርሃ ግብሩ 1ሺህ 5መቶ 1ኛውን የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዓ.ወ.) መውሊድ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።
ውይይቱን የታላቁ አንዋር መስጂድ ምክትል ኢማምና የብሔራዊ መውሊድ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ሸይኽ አብዱልሐሚድ አህመድ በንግግር ያስጀመሩት ሲሆን በመድረኩ ላይ "መውሊድ በሀበሻ እና ሁለተናዊ ፋይዳው" የሚል ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ሸይኽ አብዱልሀሚድ በንግግራቸው ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሯቸው የፍትህ፣ የፍቅር እና የሰላም እሴቶች ለሀገር ግንባታና ለህዝቦች አብሮነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ጠቅሰዋል።
ሸይኽ አብዱልሀሚድ አክለውም መውሊድ ማህበራዊ አንድነትን፣ አብሮነትን እና የእርስ በርስ መደጋገፍን ያጠናክራል ብለዋል።
ዶክተር እድሪስ ሙሀመድ በዚሁ መድረክ ላይ ባቀረቡት "መውሊድ በሀበሻ እና ሁለተናዊ ፋይዳው" የተሰኘ ጥናታዊ ፅሁፋቸው መውሊድ በሀበሻ ምድር ያለውን ታሪካዊ አመጣጥ፣ እና ሁለተናዊ ፋይዳ አብራርተዋል።
የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም፣ ኻጢብና የብሔራዊ መውሊድ በዓል ኮሚቴ አስተባባሪ ሸይኽ ጧሀ ሙሀመድ ሀሩን በጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማ ጉባዔ የፈተዋ ኮሚቴ አባልና የሀላል ዘርፍ ኃላፊ ሸይኽ አህመድ አወሉ፣ የአዲስ አበባ እስልምና ከፍተኛ ምክር ቤት የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሸይኽ ኑርሁሴን ሸይኽ ሙስጠፋን ጨምሮ መሻዒኾች እናጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በውይይቱ ላይ ታዳሚ ሆነዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት

August 23, 2026 2K 6