በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የምስራቅና መካከለኛ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ቀጣና ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።
በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ምስራቅና መካከለኛ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ቀጣና ጠቅላላ መሪዎች ጉባኤ አስሩም የቀጣናው ተሳታፊ ክልሎች በተገኙበት ከነሐሴ 25_26/2018 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።
በጉባኤው ከዋናው ቢሮ መጋቢ ንጉሴ በቀለ እና መጋቢ ተመስገን መንገሻ ሲገኙ የዕለቱ ፕሮግራም በፀሎት ፣ ዝማሬ እና የእግዚአብሔር ቃል ተጀምሯል። መጋቢ ንጉሴ በቀለ "የእግዚአብሔርን ጦርነት እንዋጋ" በሚል ርዕስ ከ2ኛ ነገ. 4፥13-22 መነሻ በማድረግ የእግዚአብሔር ቃል አቅርበዋል።
በመቀጠልም በጉባኤው የ2018 በጀት አመት የሥራ እና ሂሳብ ሪፖርት እንዲሁም የ2019 በጀት አመት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። በተጨማሪም የጊዜያዊ ቀጣናው የአምስት ዓመት ስልታዊ ዕቅድ በዝርዝር ቀርቦ ሲጸድቅ ጉባኤው በሌሎች ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
መረጃዉ ፦የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነዉ
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ
የ Evangelical Media/Council የዩቲዩብ ቻናልን
ሰብስክራይብ ለማድረግ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
• YouTube: https://youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
• TikTok: https://www.tiktok.com/@evangelical.media
• Telegram: https://t.me/EGBCC
• Website: ecgbc.org
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!
ለዜና ሽፋን መልአክት ለመላክ
t.me/evangelicalmedia
📞251 991827226 ላይ ያገኙናል
4September 2, 2026 621



