ሆሊስቲክ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ በ4ኛው ዙር 200 ተማሪዎችን በታላቅ ድምቀት አስመረቀ
ሆሊስቲክ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ከዲፕሎማ እስከ ማስተርስ ፕሮግራም በቲዎሎጂ ትምህርት ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን 200 ተማሪዎች ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት አስመርቋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የሚሽን እና የቲዎሎጂ መምሪያ ኃላፊ ፓስተር ይልማ ዋቄ በበኩላቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በመስተላለፊ ስለ ካውንስሉ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ተመራቂዎች የተጣለባቸውን አደራ በትጋት እንዲወጡ አሳስበዋል።
የኮሌጁፕሬዚዳንት ዶ/ር አንዷለም ጌታቸው ባደረጉት ንግግር፤ ለተመራቂዎች፣ ለቤተሰቦቻቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።በመቀጠልም ተመራቂዎቹ በኮሌጁ ቆይታቸው የተሰጣቸውን አደራ በጥንቃቄ እንዲጠብቁና በተግባር እንዲኖሩት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ቄስ ዶክተር ጎፈሬ አዲሾ ለተመራቂዎችና ለቤተሰቦቻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ “በአዲሱ ምዕራፍ ምን ታደርጋላችሁ?” በሚል ርዕስ በጥልቀት የእግዚአብሔርን ቃል ለተመራቂዎች አካፍለዋል።
በምረቃ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የሚሽን እና የቲዎሎጂ መምሪያ ኃላፊ ፓስተር ይልማ ዋቄ፣የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ቀጠና ዋና ጸሐፊ መጋቢ በለጠ አጀሮ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
8
8
7
1
1August 29, 2026 1.5K 5







