የዜማ ዮሐንስ አገልግሎት በመስከረም ወር አጋማሽ ታላቅ የመዝሙር ኮንሰርት ሊያካሂድ ነው
ቤተክርስቲያንን በዝማሬ ለማነጽ እና የወጣቶችን መንፈሳዊ ጸጋ ለማውጣት የሚሰራው «የዜማ ዮሐንስ» አገልግሎት በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ታላቅ የመዝሙር ኮንሰርት ሊያካሂድ መሆኑን ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዩጎሲ ቤተክርስቲያን በነበረዉ መግለጫ ላይ አስታወቀ።
የዜማ ዩሐንስ አገልግሎት አገልግሎቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ የመዝሙር መድረኮችን ሲያዘጋጅ የቆየ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በአሜሪካ 18 ግዛቶች፣ በካናዳ 5 ግዛቶች፣ በአውስትራሊያ እንዲሁም እንደ እንግሊዝ፣ ስዊድን፣ ጀርመን፣ ዴንማርክ፣ ሆላንድ፣ ስዊዘርላንድ እና ኖርዌይ ባሉ የአውሮፓ ሀገራት መንፈሳዊ ፕሮግራሞችን አካሂዷል።
የዜማ ዮሐንስ ራዕዩ ከተፀነሰ 10 ዓመታት የሞላው ሲሆን፣ ከዛሬ 5 ዓመት በፊት «ዜማ ዮሐንስ Instruments» የተሰኘውን የሙዚቃ አልበም በመስራት በይፋ አገልግሎቱን መጀመሩ ይታወቃል።
አሁን ደግሞ በዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን ከኤልቬዜት ጋር በመተባበር በመስከረም ወር አጋማሽ በሚካሄደው በዚህ ታላቅ የጉባኤ መድረክ ላይ በርካታ ዘማሪያን እንደሚገኙ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ሙዚቀኛ ዮሐንስ ዋቃጋሪ ለተደረገለት ደማቅ አቀባበል የተሰማውን ደስታ ገልጾ፣ ለዝግጅቱና ለአቀባበሉ ድጋፍ ላደረጉ አካላት በሙሉ የከበረ ምስጋናውን አቅርቧል።
በመስከረም ወር አጋማሽ በሚካሄደው በዚህ ታላቅ የመዝሙር ኮንሰርት ላይ ምዕመናን ታድመው የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
ለኢቫንጀሊካ ዜና ሩት ዋቅጅራ
7September 1, 2026 579 5


