ኢየሱስ ይመጣል በሚል መሪ ቃል በሻኪሶ ከተማ የጀማ ወንጌል ስብከት ተካሄደ። በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ… — የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC — TG.ME

ኢየሱስ ይመጣል በሚል መሪ ቃል በሻኪሶ ከተማ የጀማ ወንጌል ስብከት ተካሄደ።

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ምሥራቅ ጉጂ ጊዜያዊ ክልል ስር የምትገኘው የሻኪሶ አጥቢያ በሻኪሶ ከተማ ምዕመናን ያሳተፈ ከተማ አቀፍ የጀማ ወንጌል ስብከት አካሄደች።

ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም "ኢየሱስ_ይመጣል" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ታላቅ የጀማ ወንጌል ሥርጭት የመንግሥቱ ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሲሰበክ ብዙዎች ወንጌል ሰምተዋል፤ ንስሐ የገቡም መኖራቸው ተገልጿል።

ይህ ከተማ አቀፍ የወንጌል ስብከት አጥቢያዋ ከነሐሴ 18-22/2018 ዓ.ም አንድ ለአንድ ያካሄደችው የወንጌል ምስክርነት ሳምንት መዝጊያ ፕሮግራም ነው።

"እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።" ራእይ 22፥12
መረጃዉ፦ የመሰረተ ክርቶስ ቤተክርስቲያን ነዉ

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

የ Evangelical Media/Council የዩቲዩብ ቻናልን
ሰብስክራይብ ለማድረግ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
• YouTube: https://youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
• TikTok: https://www.tiktok.com/@evangelical.media
• Telegram: https://t.me/EGBCC
• Website: ecgbc.org
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!
ለዜና ሽፋን መልአክት ለመላክ
t.me/evangelicalmedia
📞251 991827226 ላይ ያገኙናል
🔥5❤4
August 31, 2026 1.2K