ጋብቻን ማስመዝገብ ያለበት ማን ነው?
***********************************
ጋብቻው የተፈፀመው በክብር መዝገብ ሹም ፊት ከሆነ የክብር መዝገብ ሹም ጋብቻውን ወዲያውኑ መመዝገብ አለበት፡፡
ጋብቻው በሀይማኖታዊ ወይም በባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ እንደሆነ ተጋቢዎቹ በዚህ አዋጅ (1370/2017) ፴፬ የተመለከተውን ማስረጃ ለክብር መዝገብ ሹም በማቅረብ ጋብቻውን ማስመዝገብ አለባቸው፡፡
በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፪) የተደነገገው ቢኖርም በህግ አግባብ ከተፈቀደ ከሁለቱ ተጋቢዎች አንደኛው ተጋቢ ወይም ተወካይ ጋብቻው ከተፈፀመ በኋለ ህጋዊ ውክልና ይዞ በመቅረብ ጋብቻውን ማስመዝገብ ይችላል፡፡
ጋብቻው በእንደራሴ የተፈፀመ ከሆነ ከሚመለከተው የፍትህ አካል ማስረጃ በማቅረብ ከተጋቢዎቹ አንደኛው ቀርቦ ጋብቻውን ማስመዝገብ ይችላል፡፡ ጋብቻ በተፈጸመ 30 ቀናት ውስጥ በአቅራቢያ በሚገኝ የምዝገባ ጽ/ቤት በወቅቱ አስመዝግበው በነጻ የምስክር ወረቀት ይውሰዱ፡፡
ራዕያችን:- "ዓለም አቀፍ ደረጃውን ያሟላ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ሥርዓት ተፈጥሮ ማየት!"
የአብክመ ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ህ/ግ/ዳይሬክቶሬት
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም
November 21, 2026 55