ዓለም አቀፍ የህጻናት ቀንን ምክንያት በማድረግ በደብረታቦር ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች ንጉሴ አየለ የቅድመ ልጂነት ትምህርት ቤትን ጎበኙ፡፡
“ትኩረትና እንክብካቤ ለሁሉም ህጻናት” በሚል መሪ ቃል በዓለም ለ37ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ21ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት የተከበረውን ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀንን አስመልክቶ በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ እና ፊታውራሪ ገብርየ ክፍለ ከተማ አስተባባሪነት ተማሪዎች ንጉሴ አየለ የቅድመ ልጂነት ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ህጻናት ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ንጉሴ አየለ የቅድመ ልጂነት ትምህርት ቤት በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር የሚገኝ ዶ/ር ሄዋኔ ንጉሴ በተባለች በውጭ ሀገር የምትኖር በጎ አሳቢ ግለሰብ የተቋቋመ ሲሆን ድጋፍ የሚሹ አስራ አራት የአካል ጉዳት፣ ሌሎች የጤና እና የአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናትን ጨምሮ 144 ህጻናትን በቀን ሁለት ጊዜ የሚመግብ ትምህርት ቤት ነው፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም
November 20, 2026 88 1