አንድ ሰው መደበኛ የቤተሰብ አባል ነው የሚባለው ቢያንስ ስድስት ወር ሙሉ ያለማቋረጥ ከቤተሰቡ ጋር የኖረ እንደሆነ ነው።
ከቤተሰቡ ጋር ለዘለቄታው ለመኖር የመጡ ሁሉ ከቤተሰቡ ጋር መኖር ከጀመሩ ስድስት ወር ባይሞላቸውም እንደ ቤተሰቡ መደበኛ አባል ይቆጠራሉ።
ከስድስት ወር በታች ከቤተሰቡ ለጊዜው ተለይተው የቆዩ የቤተሰብ አባላት እንደ መደበኛ የቤተሰቡ አባል መቆጠር አለባቸው።
ነገር ግን ከቤተሰቡ ተለይተው ከሄዱ ስድስት ወር ወይም ከዚያ በላይ የሆናቸው ወይም ከስድስት ወር በላይ ለመቆየት አቅደው የሄዱ ከቤተሰቡ ከወጡ ስድስት ወር ባይሞላቸውም እንደ ቤተሰቡ መደበኛ አባል አይቆጠሩም።
ርዕያችን :- ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት ተፈጥሮ ማየት ነው።
የአብክመ ሲ/ቤ/ም/አገልግሎት
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም