ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክተናል
የለንደኑ ክለብ ቼልሲ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የምሽቱ ጨዋታ ከባድ እንደነበር ተናግረዋል።
በጣም ከባድ ጨዋታ ነበር ወሳኝ ሶስት ነጥብ ነው ያሳካነው ሲል ዣቢ አሎንሶ ተናግረዋል።
አክለውም ከሜዳ ውጪ ጨዋታዎችን ለማሸነፍ መጎዳት እና የግብ ክልልን በጥሩ ሁኔታ መጠበቅ እንዳለብን እናውቃለን ብለዋል።
ስለ ጨዋታው አንስተውም በመጀመሪያው አጋማሽ በመከላከሉ ጥሩ ያልነበርንባቸው ጊዜያት ነበሩ ሲል ተናግረዋል።
አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ስለ ኢንዞ ፈርናንዴዝ የወደፊት ቆይታ ተጠይቆ በዚህ ሳምንት እናያለን ሲል ምላሽ ሰጥተዋል።

1August 24, 2026 127 1