ፒኤስጂ ነጥብ ጥሎ ዓመቱን ጀምሯል::
በፈረንሳይ ሊግ 1 የመጀመሪያ ሳምንት መርሃግብር ከሜዳ ውጪ ተጉዞ ስታድ ሬንስን የገጠመው ሻምፒዮኑ ፓሪስ ሴንት ዤርመን ከሁለት ለዜሮ መመራት ተነስቶ 2ለ2 በሆነ ውጤት ጨዋታውን ማጠናቀቅ ችሏል:: ስታድ ሬኖች እስከ 70ኛው ደቂቃ ድረስ 2ለ0 መሪ የነበሩ ቢሆንም በእረፍት ኦስማን ዴምቤሌን ቀይሮ ወደሜዳ የገባው አዲሱ ፈራሚ ፌራን ቶሬስ በ71 እና 82ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ሌፓሪዛውያኑን ከሽንፈት ታድገዋል::



















