📌እንኳን ደሳለን!
የአርሰናል የዋንጫ ድል እንደ ተራ የስፖርት ድል ብቻ የሚታይ አይደለም። የአርሰናል የቅርብ ጊዜ ጉዞ በተለይም ለዓመታት ከጫፍ ደርሰው ዋንጫ ሲያመልጣቸው የነበረው ውጣ ውረድ፣ በስህተት ላይ ስህተት ሲሠሩ የነበሩበት ጊዜያት፣ እንዲሁም በደጋፊና በባለሙያዎች የተሰነዘረባቸው የማያባራ ትችት ከማንኛውም የህይወት ትግል ጋር በሚገርም ሁኔታ ይገናኛል።
አርሰናል ዋንጫ ያነሳው በሌሊት ተነስቶ አይደለም። የተገኘው ድል የረጅም ዓመታት መዋቅራዊ ለውጥ ውጤት ነው። በህይወትም ውስጥ ልንማረው የሚገባን ቁምነገር ይህ ነው። ብዙ ጊዜ የድል አቅጣጫው ሲዘገይ ወይም ፈተናዎች ሲበዙ፣ ድካምና ተስፋ መቁረጥ ይፈጠራል። ነገር ግን አርሰናል "አይቻልም" በተባለበት ወቅት፣በታታሪዎች እየተገነባ ዛሬ ውጤቱን አሳይቷል።
የአርሰናል ድል 3 መሰረቶች አሉት ፦
1. የጽናት ውጤት፡ አርሰናል በሽንፈት ውስጥም ቢሆን የራሱን የጨዋታ ፍልስፍና አልለቀቀም።
2. መዋቅራዊ አንድነት፡ የአርሰናል ድል የተገኘው የቡድን አባላቱ በአንድነት በመሰለፋቸው ነው።
3. ከስህተት መማር፡ አርሰናል ባለፉት ዓመታት የፈጸማቸውን ስህተቶች በማረም ነው ወደሚፈለገው የድል ግብ መድረስ የቻለው።
የአርሰናል የዋንጫ ድል ማሳያው "መታገልና መታገስ ዋጋ አለው" የሚለውን ነው።
እንኳን ደስ አለን በድጋሚ!

4
2
1
1May 20, 2026 410 1