ጀንበር የቀደሙ መሪዎቻችንን ቀይጠን ምን ማውጣት እንችላለን? ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተቋም የመገንባት ክህሎት፣… — ❤️City of life❤️ — TG.ME

📌 ጀንበር
የቀደሙ መሪዎቻችንን ቀይጠን  ምን ማውጣት እንችላለን?
ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተቋም የመገንባት ክህሎት፣ ከርሳቸው በእውቀት የሚበልጡ የካቢኔ አባላትን የማዋቀር ፍላጎትን እና በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ያላቸውን ተቀባይነት ብንወስድ፤
ከመንግስቱ ኃይለማርያም ሙስና ውስጥ አለመነከርን፣ የፊውዳል የመሬት ሥሪትን ማሶገድን እና ዘረኛ አለመሆንን፣ ድህነትን ለማስወገድ የነበረው የፖሊሲ ጥራት እና ትግበራን ብንቃርም፤
ምን አይነት ኢትዮጵያ ትፈጠር ነበር?

ጀንበር በተሰኘው ነጠላ ዜማው ቴዲ አፍሮ
በጊዜያቸው ተፃራሪ የነበሩ የሁለት መሪዎችን አሻራ በአንድነት አስመልክቶናል።

"ማናቸውም ኢትዮጵያዊ ትክክል መብት እንዲኖረውና የተወደደው ህዝባችን ሁሉ የአንድ ትልቅ ቤተሰብ ተወላጅ ሆነው በወንድማማችነት እንዲኖሩ ዘወትር የተከተልነው አላማ ነው።"
ይህንን ከቀዳማዊ ሃይለስላሴ ንግግር ፤
ፀሀዬ ደመቀች እና ኢትዮጵያ ትቅደምን
ከመንግስቱ ሀይለማርያም አሻራዎች በመውሰድ ፤
ሀለዎቴ የልቤ ትርታ አመላክቺኝ ሀቅ ያለው ቦታ..... ብሎ አንጎራጉሮልናል።
በመቀጠልም "አሁን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከንጋቱ 11 ሰዓት ነው" በማለት ኢትዮጵያ የንጋት ጮራዋን እንደምታይ አመላክቷል የዘፈኑንም ማሳረጊያም ይኸንኑ የተስፋ ቃል አድርጎታል ።
❤8
April 16, 2026 513