ትናንት አንድ ሽልጥልጥ ወንድ አጋጥሞኝ አንጀቴ ተቃጥሎ ነበር የዋልኩት። ወንድ እንደወንድነቱ እንጂ በሴቶች ለመወደድ የማይሆን ሴታሴት ባህሪ ሲያሳይ ዓሳ እንደሚያድን የጫካ ሰው በጦር ውጋው ውጋው የሚል ስሜት ነው የሚፈጥርብኝ። ልጁ ወጣት ነገር ነው። ችግሩ እሱ አይደለም። ችግሩ ሴቶችን አለቅጥ ማወደስና ወንዶችን ማጥላላት የሚወድ ቫፋንኩሎ ነገር መሆኑ ነው!። በዛ ላይ ፌሚኒዝምንን እንደሃይማኖት የሚሰብክ ቆለጥ አይን ጭምርም ነው። እኔም የዋዛ አይደለውም አንገት እስከመታነቅ የሚያደርስ ሎጃካሊ ስድብ ሰድቤው ልብስ ተያያዝን። በርግጥ አያገባኝም ነበር። ነገር ግን ሴቶች እንዲስቁለት በእኔ ላይ ሙድ ለመያዝ ሲሞክር መጀመርያ ሙዝ በመያዝ ጠግቦ ማደር እንዳለበት አስረግጬ ነገርኩት።
በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ወንዶች «Morality as a Mask, Equality as a Strategy» የሚል ስያሜ የሚሰጣቸው ወንድም ሴትም ያልሆኑ አዲስ ፍጡሮች ናቸው። Morality as a Mask, Equality as a Strategy ማለት ሞራልን እንደ ጭንብል፣ እኩልነት እንደ ስትራቴጂ የሚጠቀሙ የሰው ዓይነቶች ናቸው። በነገራችን ላይ እዚህ ጋር ፌሚኒዝምን የሚደግፍ ሰው ለመውቀስ አስቤ አይደለም። እኩልነትን መደገፍ በራሱ ችግር አይደለም፤ ችግሩ የሚጀምረው አንድ ሰው እኩልነትን እንደ እኩልነት ማሰብ ሲያቆምና እንደ መሳሪያ መጠቀም ሲጀምር ነው። ያኔ ነው ሞራል ወይም ስነምግባር ከውስጣዊ መርህ ወደ ውጫዊ ፍላጎት የሚቀየረው። እኩልነትም ከፍትህ ጥያቄ ወደ ግል ጥቅማጥቅ ይለወጣል።



