አይሲድ_ከበሌ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ጉባ ወረዳ መከተል ዞን የካቲት 24 በ2014 ዓ.ም ሰውን በእሳት እያቃጠሉ… — አርምሞ🧘🏽‍♂ — TG.ME

#አይሲድ_ከበሌ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ጉባ ወረዳ መከተል ዞን የካቲት 24 በ2014 ዓ.ም ሰውን በእሳት እያቃጠሉ ቪድዮ ቀርጸው የለቀቁ የወታደር ልብስ የለበሱ አካላት ናቸው። EHRC በዜና አርቲክሉ ላይ እንደዘገበው 11 ሲቪሎች በደህንነት ኃይሎች ከተገደሉ በኋላ አስከሬኖቻቸው ተቃጥለዋል፤ ከእነሱ መካከል አንዱ በሕይወት እያለ ታስሮ ወደ እሳት እንደተጣለ የተመረመረው ሪፖርት አረጋጧል። Ethiopia Insight ሆነ የUN ሰነድም የተለያዩ ምንጮችን ጠቅሶ በዚያኑ ቀን ሰዎችሁ ተይዘው ክፉኛ ተደብድበውና ተገድለው እንደተቃጠሉ፤ ከዚያም አንድ ሰው በሕይወት እያለ እንደተቃጠለ ከግፍ ፈጻሚዎችሁ የቪድዮ ቅጂ ማረጋገጥ ተችሏል

#የ2014ቱ_የታህሳሱ_ጭፍጨፋም ሌላ ትኩሳት ነው። ይሄም እንደሌሎችሁ የቪድዮ ቅጂ ያለው ሲሆን ቦታ ከቪድዮው ጥራት አንፃር በውል ባይታወቅም በድጋሚ በ2015 ዓ.ም መሰል ቪድዮዎች በየቦታው ተሰራጭተው ለመታዘብ ችለናል። ቪድዮው ላይ የወታደራዊ ልብስ የለበሱ ግለሰቦች ከመኪና ላይ ሰዎችን አስወርደው ሲረሽኗቸው ያሳያል። EHRC ቪድዮው ላይ ምርመራ በማድረግ ቢያንስ ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎች በጅምላ extrajudicial killing እንደተፈጸመባቸው አሳውቋል።

አያችሁ ይህ ሁሉ ጭፍጨፋ ያስተናገዱት ወታደሮች እርስ በእርሳቸው ተዋግተው ሳይሆን ምንም የማያውቁ ንጹሃን ተጠርተው ነው። በእኛ ሀገር ጦርነት ተዋጊውን ሲገድል እንብዛም አይታይም። ይልቅስ በብዙ ግጭቶች ውስጥ የሚገደሉት ሰዎች በግጭቱ ውስጥ ምንም ድርሻ የሌላቸው ሲቪሊያንስ ናቸው። ምክንያቱም ጦርነቱ ከግለሰቦች ጋር የሚፈጠር ግጭት ሳይሆን ቡድኖችን ግምት ውስጥ የሚያስገባ አካሄድ ነው። አንድ ሰው በተወለደበት ቦታ፣ በቋንቋው፣ በብሔሩ ወይም በማንነቱ ብቻ «የጠላት አካል» ተደርጎ ይወሰዳል።

በነገራችን ላይ ይህን ሁሉ በቀላሉ የጦርነት አሰቃቂነት አልለውም፤ የሰዎች መመናመን ብቻም አይባልም፣ ይልቅስ ይህ የሰውነት ትርጉም መጥፋትም ጭምር ነው። እኔ በበኩል እንዲህ ዓይነት ፎቶዎች፣ ዜና እና ቪድዮዎችን ማየት አቁሚያለሁ። እንደዚህ ዓይነት የግፍ ፎቶ ሲለጠፍ አዕምሮዬ ላይ ቀጥታ የሚመጣው፦
«የሳምንት አጀንዳ» የሚለው ምፀት ነው!።

አንድ ማኅበረሰብ እንዲህ አይነት በደሎችን ማየት ሲያበዛ ግፍ በሰው ዓይን ውስጥ ከአሰቃቂነቱ ወደ ተለመደ ነገር መለወጥ ይጀምራል። የአንድ ሀገር ትልቁ አደጋ ሰዎች መሞታቸው ብቻ አይደለም፤ ሰዎች ሌሎች ሰዎች ሲሞቱ ምንም ሳይሰማቸው መቅረቱ ነው። ያኔ ጦርነት ከመሬት ግጭት ወጥቶ ወደ ሰው ነፍስ ይገባል!። የሰዎችም ሞት የቁጥር እና የቃላት ማዳመቂያ የሳምንት አጀንዳ ሆኖ ይቀራል!። ከዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ በኋላ ሀገራችን ሰላም ትሆናለች ብሎ እንደሚያስብ አማኝ ጥሬ የለም!። ከዚህ በኋላ ከዚህም የበሳ እንጂ የሚበርድ እሳት የለም!። አዲስ አበቤም በቅርቡ ጠብቂ የደም ምድር..
!


@Armemo_offical
💔18😢2👍1
August 30, 2026 949 2 6