ዛሬ በዚህ ጉዳይ የመጨረሻ ፖለቲካል አርቲክሌ ነው። ስለዚህ እስከመጨረሻው በማንበብ እንሰነባበት። መጻፉ ላይ… — አርምሞ🧘🏽‍♂ — TG.ME

ዛሬ በዚህ ጉዳይ የመጨረሻ ፖለቲካል አርቲክሌ ነው። ስለዚህ እስከመጨረሻው በማንበብ እንሰነባበት። መጻፉ ላይ ልምድ ቢኖረኝም መረጃ ለማሰባሰብና የመረጃውን ተአማኒነት ለማረጋገጥ ግን ብዙ ሰዓት ፈጅቶብኛል። ስለዚህ ላይክ በማድረግ ጀምሩ።

በሀገራችን ኢትዮጲያ ጦርነት የተለመደ አሳዛኝ ክስተት ነው። በተለይ ከደርግ እስከ ኢሕአዴግ ብዙ የእርስ በእርስ ጦርነቶችን አስተናግደናል። ነገር ግን ከ2010 በኋላ የመጣው የሽግግር መንግስት ተከትሎ ታይቶ የማይታወቅ የሰብዓዊነት ጭካኔ በሀገራችን ኢትዮጲያ ተፈጽሟል።
ይህ የጭካኔ አካሄድ የተለመደ ነገር ቢሆን ፖለቲካዊ ሰብዓዊነትን በመንፈግ ጥቃትን ወደ ትዕይንት በመቀየር ፎቶ እና ቪድዮ ሰርተው የሚለቁ አውሬዎች መብዛታቸው ያስደነግጣል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2020 እስካለንበት 2026 ድረስ ግፍን መስማት የተለመደ ነገር ሆኗል። ከዛ በላይ ግን ግፍን ወደ ቪድዮ ቀይሮ በሶሻል ሚዲያ ፖስት የሚያደርጉ ሰዎች መብዛታቸው ብቻ ሳይሆን ያንን ቪድዮ እና ፎቶ ደጋግሜ ማየቴ የአዕምሮ ቀውስ ውስጥ አስገብቶኝ ነበር። እንዲህ አይነት የጭካኔ ትዕይንት በሱዳን እና መሰል ጎረቤት ሀገሮች ላይ የሚፈጸም በፖለቲካ አጠራሩም
«Political Dehumanization and the Spectacle of Violence» ይባላል።

በሀገራችን ኢትዮጲያ ሰዎችን በገጀራ እያረዱ ቪድዮ የሚቀርጹ፣ ሰዎችን እየረሸኑ የሚቀርጹ፣ ሰውን ከእነህይወቱ በእሳት እያቃጠሉ ቪድዮ የሚቀርጹ ነብሰ በላ ሰዎች ማየት የተለመደ ከሆነ ሰነባብቷል። ክስተቱም «የአንድ ሳምንት አጀንዳ» ነው። ቢሆንም ይህንን ጭካኔ ብሎ ብቻ መግለጽ በቂ አይሆንም። ይልቅስ በፖለቲካል ሳይኮሎጂ ከሚጠቀሱ ጽንሰ-ሐሳቦች መካከል
Moral Disengagement ጭምር ነው።
😢8💔8❤5👍3👏2
August 30, 2026 882 6