ይህ የፖለቲካ ሳይኮሎጂ ሰውን «ወንጀለኛ» ወይም «ክፉ» ብሎ መጥራት በእሱ ላይ የሚደርስበት ግፍ እንደመደበኛ… — አርምሞ🧘🏽‍♂ — TG.ME

አርምሞ🧘🏽‍♂ዛሬ በዚህ ጉዳይ የመጨረሻ ፖለቲካል አርቲክሌ ነው። ስለዚህ እስከመጨረሻው በማንበብ እንሰነባበት። መጻፉ ላይ ልምድ ቢኖረኝም መረጃ ለማሰባሰብና የመረጃውን ተአማኒነት ለማረጋገጥ ግን ብዙ ሰዓት ፈጅቶብኛል። ስለዚህ ላይክ በማድረግ ጀምሩ። በሀገራችን ኢትዮጲያ ጦርነት የተለመደ አሳዛኝ ክስተት ነው። በተለይ ከደርግ እስከ ኢሕአዴግ ብዙ የእርስ በእርስ ጦርነቶችን አስተናግደናል። ነገር ግን ከ2010 በኋላ…
ይህ የፖለቲካ ሳይኮሎጂ ሰውን «ወንጀለኛ» ወይም «ክፉ» ብሎ መጥራት በእሱ ላይ የሚደርስበት ግፍ እንደመደበኛ ወይም እንደምክኒያታዊነት እንዲቀበሉት የማድረጊያ ሲስተም ነው። «ሁለት ፋኖዎች ዛሬ ገድለናል፣ አራት ጁንታዎች ተረሽነዋል፣ አንድ ክፈለ ጦር ሸኔ ደምስሰናል!» የሚለው የስም ታፔላ የሟችሁን ሞት ዋጋ የሚያሳንስ Dehumanization ነው። ሌላውን ሰው እንደ ሙሉ ሰው ማየት ሲቀር ሞታቸው «እነሱ» የሚል የቁጥር ስያሜ ተሰጥቶት ዋጋ ያለው ክብር ህይወትን የማሳነስ እስራቴጂ ነው። በጁንታው እና በፋኖ ከለላ ስማቸው፣ ቤተሰባቸው፣ ሕልማቸው፣ ፍርሃታቸው እና ሕይወታቸው በሌላ ሰው ዓይን ይረክሳል። ያኔ ነው ሰውን መግደል እንደነፍስ ማጥፋት ከማሰብ ይልቅ ጠላትን ማስወገድ መስሎ እንዲሰማን የሚያደርገን።

ቅርብ ግዜ የተከሰተው ፋኖ ናችሁ በሚል የተረሸኑትና አስከሬናቸውም እንዳይነሳ ለቀናት የተከለከለው ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው፣ ግዛው ግርማዬ እንደምሳሌ ማየት በቂ ነው። እንዲህ አይነቱን የፖለቲካ ስልት ማወቅ ከፈለጋችሁ
«Social Identity» ቲዎሪን ሰርች አድርጋችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። የሰው ልጅ ማንነት «እኛ» እና «እነሱ» በሚል ጎራ ሲከፈል የሌላው ቡድን ሕይወት ከእኛ ሕይወት ያነሰ ዋጋ ያለው እንደሆነ የሚያስብ አደገኛ የሞራል ልዩነት በማኀበረሰቡ ዘንድ ሊፈጠር ይችላል።

ይህ
Collective Punishment አንድ ሰው ወይም አንድ ቡድን በፈጸመው ነገር ተነሳስተው ከግጭቱ ጋር በቀጥታ ያልተያያዙ ሰዎችን የመቅጣት ሰይጣናዊ አካሄድ ነው። እንዲህ አይነቱ ግፍ በጦርነት ውስጥ ከሚከሰቱት እጅግ አደገኛ የጭፍጨፋ መዋቅሮች አንደኛው ነው። ቢሆንም ግን ቪድዮ መቅረጹ ደግሞ ሌላ የአረመኔነት ደረጃ ነው። ይሄም ከላይ እንደጠቀስኩት «Spectacle of Violence» ወይም «የግፍ ትዕይንት» ይባላል። ግፍ ከተፈጸመ በኋላ ማስረጃ ለመያዝ ብቻ ሳይሆን ለማስፈራራት፣ ለማዋረድ፣ ለማሳየት እና «እኛ እንዲህ ማድረግ እንችላለን» የሚል የኃይል መልዕክት ለማስተላለፍ በሞተ ሬሳ ላይ ቪድዮ እንደመስራት ያለ ሌላ የፖለቲካ መልዕክት ጭምር ነው። ሰዎችን መግደል የተለመደ ግፍ ቢሆንም የሞቱትን አስከሬን ለሌሎች ለማስፈራራት ማሳየት ግን ግፉን ወደ terroristic communication ይቀይረዋል። በቪድዮው ላይም ለማስተላለፍ የሚፈልጉት፦«እኛን ብትቃወሙ ይህ ይደርስባችኋል» የሚል መልዕክት ነው።

በተደጋጋሚ በሶሻል ሚዲያ ላይ እንዲህ ዓይነት መሰል ቪድዮዎች ሲሰራጩ የሰው ልጅ ነፍስ እንዲረክስ ምክንያት ሆኖታል። መጀመሪያ ሊገደል የታሰበውን ሰው ከሰውነቱ ማስወጣት፤ ቀጥሎ ደግሞ ስሙን «ሸኔ እና ፋኖ» በሚል መለያ መተካት፤  ከዚያ «ጠላታችን» ነው ማለት፤ በመጨረሻም ሰለባ የሆነውን ሰውዬ እንደተራ ነፍስ በማየት መግደል። ታድያ ማኀበረሰቡ ሌላውን ሰው እንደ ሰው ማየት በሚያቆምበት ቅጽበት ግፍን የሚቃወምበት የሞራል ግድግዳው ይፈርሳል። ከዚያ በኋላ ግን ገጀራው ሳይሆን ሀሳብ ነው መሳርያ የሚሆነው። ጥይቱ ብቻ አይገድልም፤ የተዛባው ማንነት ጭምር ነው ገዳይ የሚሆነው። እሳቱ ሰውዬውን ብቻ አያቃጥለውም፤ ይልቅስ የሰውን ሕይወት ዋጋ የሚያሳንሰው ርዕዮተ ዓለም ጭምር ነው አብሮ የሚቃጠለው። እነዚህ ከስር ያስቀምጥኳቸው በሀገራችን ኢትዮጵያ የተከሰቱ የቪድዎ እና የፎቶ ማስረጃ ያላቸው ጭፍጨፋዎች ናቸው። ያልተዘገቡት ደግሞ ከዚህ የበለጡ እንደሆነ ልቦናችን ያውቀዋል።


#ማይካድራ በ2013 ዓ.ም ጥቅምት 30 በማይካድራ ምዕራብ ትግራይ የተፈጸመው መቼም ከልባችን የማይወጣ ክስተት ሆኖ ነው ያለፈው። በትግራይ ጦርነት መጀመሪያ ወራት አካባቢ ከተፈጸሙ እጅግ አስከፊ ጭፍጨፋዎች አንዱ ነው ሊባልም ይችላል። በዛ ወቅት የተፈጠረውን ክስተት «Amnesty International» በድህረ ገፁ የፎቶ እና የቪድዮ ማስረጃ አስቀምጦለታል። በቪድዮ እና በፎቶ ባስቀመጠው ዜና ላይም በውድቅት ሌሊት ብዙ ሰዎች በቢላዋ፣ በገጀራ እና በሌሎች ስለታም መሣሪያዎች እንደተገደሉ ዘግቧል። ከዚህ ሌላም ሰፊ ምርመራም በማካሄድ በማይካድራ የአማራ ሲቪሎች በገጀራ፣ በመጥረቢያና በሌሎች ባህላዊ መሣሪያዎች መገደላቸውን ዝርዝር መረጃ አውጥተዋል። (source፦Amnesty International UK
Human Rights Watch እና Amnesty)

#ማህበረ_ደጎ በ2013 በጥር እና በታኅሣሥ ወራቶች በትግራይ አካባቢ የተከሰተ ሌላኛው አሳዛኝ ክስተት ነው። ማስረጃውም Bellingcat ከBBC Africa Eye እና Newsy ጋር ተጣምሮ በመስራት አምስት ቪድዮዎችን በgeolocation አውጥቷል። ቪድዮዎቹም ወታደራዊ ልብስ የለበሱ ሰዎች ሲቪሎችን እየገደሉ የሚያሳይ ሲሆን፤ ክስተቱም በ2013 ጥርና ታህሣሥ ወር ላይ በማህበረ ደጎ አካባቢ መከሰቱን ምርመራው አረጋግጧል።

#አክሱም ላይ በተመሳሳይ አመት ከህዳር 19 እስከ 20 ባሉት ወቅቶች የኤርትራ ወታደሮች ምንም ያልታጠቁ ሲቪሎችን በጎዳናዎች ላይ እና በቤት ለቤት ፍተሻ በማካሄድ እንደጉድ የትግራይ ንጽሃንን እየጨፈጨፉ እንደነበር Amnesty International ዘግቧል።
💔12😢3❤1👍1
August 30, 2026 818 5