እስራኤል አሁንም ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣት እቅድ እንዳላት የመከላከያ ሚኒስትሩ አስታወቁ ሐሙስ፣ ነሐሴ… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
እስራኤል አሁንም ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣት እቅድ እንዳላት የመከላከያ ሚኒስትሩ አስታወቁ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 28  ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)

የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ፤ ሀገራቸው አሁንም ቢሆን ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለቅቀው እንዲወጡ ወይም የማስወጣት ፍላጎት እንዳላት ተናገሩ።

ሚኒስትሩ፤ ይህ ሳይሆን የቆየበትን ምክንያት ሲያስረዱ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ዕቅዱን ጊዜያዊ እገዳ ስላደረጉበት እንጂ አልተሰረዘም ብለዋል።

ካትዝ፤ “ዋይ ኔት” የተሸኘ የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ እንዳሉት ከሆነ  ፍልስጤማውያንን ከጋዛ  ማስለቀቅ ወይም ማጽዳት “ብቸኛውና ዘላቂው መፍትሔ” ነው።

እንደ ካትዝ ገለጻ ከሆነ፤ እቅዱ በየጊዜው ውይይት እንደሚደረግበት አንስተው፣ እቅዱም  ሙሉ በሙሉ አልተሰረዘም ብለዋል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግም የዋሽንግተን ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ያነሱት ካትዝ፤ “ያ ጊዜ ደግሞ ይመጣል”ሲሉ  ፍልስጤማውያን  ጋዛን ለቅቀው የሚወጡበት ቀን እንዳለ ጠቁመዋል።

እስራኤል ፍልስጤማውያንን በባህር፣ በአየርና በሌሎች መንገዶች ለማስወጣት ዝግጁ ብትሆንም፤ ከጋዛ ጋር የምትዋሰነው ጎረቤት ሀገር ግብፅ የፍልስጤም ተፈናቃዮችን አልቀበልም ማለቷ እና ሌሎች ተቀባይ ሀገራት የአሜሪካን ድጋፍ የሚሹ በመሆናቸው እቅዱ እንዲዘገይ እንዳደረገው ይታወሳል።

የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ይህ እርምጃ “የዘር ማጽዳት ወንጀል ነው” ሲሉ የኮነኑት ሲሆን፤ የአሜሪካው ሴናተር ክሪስ ቫን ሆለን ደግሞ፣ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ንግግርን ሀገሪቱ “የዘር ማጽዳት እቅድ እንዳላት ማረጋገጫ ነው” ሲሉ አሜሪካ ከዚህ ድርጊት ጋር ያላትን አጋርነት ማቆም አለባት ሲሉ መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።


 ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤5👎3👏1
September 3, 2026 3.3K 1 3