በኮንጎ ኢቦላ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን እንደገና በመክፈት በርቀት ትምህርት ለመስጠት ተይዞ… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
በኮንጎ  ኢቦላ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን እንደገና በመክፈት በርቀት ትምህርት ለመስጠት ተይዞ የነበረውን ደንብ መሰረዙ ተገለጸ 

ሐሙስ፣ ነሐሴ 28  ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ባደረሰባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች በዚህ ሳምንት የተከፈቱ ሲሆን  ከዚህ ቀደም ትምህርት በርቀት እንደሰጥ የነበረው ደንብ እንደተሰረዘ ተገለጸ። 

የሀገሪቱ ባለስልጣናትም የበሽታው የመተላለፍ አደጋ ተማሪዎች በርቀት ትምህርት  ሲማሩ ከሚያጋጥማቸው አደጋ ያነሰ ነው  የሚል ዉሳኔ ላይ መድረሳቸዉን አስታዉቀዋል፡፡

በሀገሪቱ በረዥም ጊዜ ታሪኳ ባጋጠማት የኢቦላ ወረርሽኝ  የሞቱ ሰዎች ቁጥ ከ3 ሺ ያለፈ ሲሆን፤ ይህ የሀገሪቱ መንግስት  ባወጣዉ መረጃ መሰረት ሲሆን በሽታው በስድስት ግዛቶች ተሰራጭቶ  የሟች መጠኑ ደግሞ 48.6 መቶ እንደሆነ ሲንቢሲ አፍሪካ ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የሀገሪቱ  የትምህርት ሚኒስቴር ሰነድ መሰረት በኢቱሪ ከ1ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች “ቀይ ዞን” ውስጥ ሲመደቡ ይህም ማለት  ደግሞ ለኢቦላ በከፍተኛ ተጋላጭ ዞን ያለበት አልያም ከፍተኛ  የመተላለፍ ሁኔታ ያለበት ቦታ ነዉ፡፡

እ.አ.አ ነሐሴ 19 ቀን 2026  የታተመው የሚኒስቴሩ ደንቦብ እንደሚያመልክተው በቀይ ዞን ያሉ ትምህርት ቤቶች የአካል ትምህርትን በጊዜያዊነት “በርቀት ትምህርት” እንደሚተኩ ደንግገዋል፡፡  ይህም በየሁለት ሳምንቱ በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን  እንደሚያካትት ተገልጻል። ነገር ግን በዚህ ሳምንት በኢቱሪ ያሉ ትምህርት ቤቶች እንደተለመደው  እንደተከፍቱ የትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናት አረጋግጠዋል፡፡ ።

በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤኤፍሲ/ኤም23 አማፂያን ባለፈው አመት በክልሉ  ባካሄዱት ፈጣን ጥቃት በቁጥጥር ስር ባሉ የሰሜን ኪቩ እና ደቡብ ኪቩ ግዛቶችም ትምህርት ቤቶች መከፈታቸዉን የአማፂያን ሀላፊዎች ገልጸዋል።  ሀላፊዎቹ በክፍሎች ውስጥ የእጅ መታጠብ እና ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅን ግድታ ማድረጋቸዉ ተጠቁሟል፡፡

ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤7
September 3, 2026 1.4K