ኤል ኒኖ በምስራቅ እና በደቡብ አፍሪካ 162 ሚሊዮን ህጻናት ላይ አደጋ መደቀኑ ተገለፀ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
በምስራቅ እና በደቡብ አፍሪካ ከ162 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ህጻናት እየጠነከረ ባለው የ2026/2027 የኤል ኒኖ ክስተት ተጽዕኖ በተጋለጡ አካባቢዎች እየኖሩ ነው ሲል የተባባሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩ.ኒ.ሴፍ) አስጠነቀቀ። ይህም በስፋራው ካሉት አጠቃላይ ህጻናት ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት ናቸው ተብሏል።
እየተባባሰ ያለው የመጣው ድርቅ በከፍተኛ ሙቀት እና ጎርፍ የህጻናትን አመጋገብ፣ ጤና፣ የንፁህ ውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ ተደራሽነት፣ ትምህርት እና ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላል ተብሏል ። ትንበያዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በጣም ከባድ መዘዞች ከመሰማታቸው በፊት እርምጃ ለመውሰድ ጠባብ ቢሆንም ወሳኝ የሆነ እድል ይሰጣሉ ተብሏል።
“ከኤል ኒኖ የሚያመጣዉ ስጋት እያደገ ሲሆን ለህጻናቱ የሚደርሰው አደጋም ቀድሞውንም ግልጽ ነው” ሲሉ የዩኒሴፍ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር ኤትሌቫ ካዲሊ ተናግረዋል።
በቀጠናዉ ውስጥ ህጻናት የምግብ እና የውሃ እጥረት እንድሁም ከአቅም በላይ የሆነ የጤና አገልግሎት ጫና እና የትምህርት መስተጓጎል እያጋጠማቸው እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም “ከባድ የአየር ንብረት ቀውሶች ህጻናትን እና እነርሱ ላይ መሰረት ያደረጉ ስርዓቶች ላይ እስከ መፈራረስ ድረስ ሊያደርሱ ይችላሉ።” ብለዋል፡፡
በዩኒሴፍ ግምገማ መሰረት በጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ ላሉ ህጻናት አስቸኳይ እና ተደራራቢ አደጋዎችን እንዳሉ አመላክቷል።
እንደምሳሌ በሶማሊያ ጎርፍ በጣም አስከፊ ሁኔታ ዉስጥ የሚገኙ እስከ 2.5 ሚሊዮን ሰዎችን በቀጥታ ሊጎዳ ይችላል ብሏል፡፡ ይህም ተጨማሪ መፈናቀልን በማስከተል የህጻናትን የምግብ፣ የጤና እንክብካቤ፣ የንፁህ ውሃ እና የትምህርት ተደራሽነት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡
ተቋሙ በተለይም በኢትዮጵያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ከፍተኛ የምግብ እጥረት እና ተጋላጭነት ባለባቸው አካባቢዎች የመጎዳት አላቸው ብሏል። አክሎም በደቡብ ሱዳን ደግሞ ኢል ኒኖ ድርቅ፣ ከፍተኛ ሙቀት እና አካባቢያዊ ጎርፍን ጨምሮ የምግብ እጥረትን አልያም የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን የበለጠ ሊባባስ ይችላል ብሏል። ይህም የበሽታ መስፋፋትን ሊጨምሩ እና የረሃብ አደጋን እና ሰፊ መፈናቀልን ሊያባብሱ ይችላሉ ብሏል።
ይሁን እንጂ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ዉስጥ ከአንድ በመቶ ያነሰ ለቅድመ ዝግጅት እርምጃ መዋል እንደሚቻል ተናግሮ ይህም የነፍስ አድን ፣ሰብዓዊ ፍላጎቶችን ለመቀነስ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ የተገኙ ውጤቶችን ለመጠበቅ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡
ዩኒሴፍ 13 ቅድሚያ በተሰጣቸው ሀገሮች ለህጻናት እና ቤተሰቦች ቅድመ ዝግጅት እና ህይወት አድን እርዳታ ለማድረስ በነባሩ እ.አ.አ በ2026 ለህጻናት ድጋፍ የሚዉል 173 ሚሊዮን ዶላር አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልገኛል ብሏል፡፡
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
9September 2, 2026 4K 4