ኖርዌይ የሩሲያን መርከብ በዩክሬን የነዳጅ ኩባንያ ጥያቄ በመያዝ ሞስኮን አስቆጣች
ዓርብ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
ኖርዌይ፤ በአርክቲክ ስትንቀሳቀስ የነበረች የሩሲያን መርከብን በዩክሬን የነዳጅ ካምባኒ ናፍቶጋዝ ጥያቄ መሰረት የያዘች ሲሆን፣ ይህም ሞስኮን ክፉኛ አስቆጥቷል ተባለ።
በአርክቲክ ስቫልባርድ በተሰኘ ቦታ ላይ በሚገኘው የባሬንትስበርግ ወደብ፣ የነበረችው ፕሮፌሰር ሞልቻኖቭ የተሰኘቸው መርከብ እንደሆነች ተገልጿል። ሩሲያ አለኝ ያለችውን አማራጭ ሁሉ ልትጠቀም እንደምትችል አስታውቃለች።
እርምጃው የተወሰደው የዩክሬን ብሔራዊ የነዳጅ እና ጋዝ ኩባንያ ናፍቶጋዝ ባቀረበው የህግ ጥያቄ መሰረት እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ የመርከብ መያዝ ከካሣ ጋር የሚያያዝ ሲሆን እ.አ.አ. በ2014 ሩሲያ፤ ክሬሚያን በኃይል በያዘችበት ወቅት፣ የናፍቶጋዝን የነዳጅ እና የጋዝ መሰረተ ልማቶች በህገ ወጥ መንገድ ስለወሰደችበት ነው ተብሏል።
በሄግ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ. በ2023 ሩሲያ ለናፍቶጋዝ 4.22 ቢሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ እንድትፈጽም ውሳኔ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።
ሞስኮ ክፍያውን ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆኗ፣ የኖርዌይ ኖርድ-ትሮሚስ እና ሴንያ የዲስትሪክት ፍርድ ቤት ከሶስት ቀን በፊት መርከቧ እንድትያዝ ትዕዛዝ አስተላልፏል ተብሏል። አሁን ላይ መርከቧ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ታወጣለች ተብሏል።
መርከቧ፤ በዋናነት ለንግድ እና ለምርምር ጉዞዎች የምታገለል ስትሆን፣ ከቦታዋ እንዳትንቀሳቀስ እገዳ ተጥሎባት በውስጧ ያሉትን ተሳፋሪዎች እና ሰራተኞች ሁኔታ የኖርዌይ ባለስልጣናት ይዘውታል ተብሏል።
የናፍቶጋዝ ኩባንያ ጊዜያዊ ስራ አስፈጻሚ፤ ሩሲያ የዓለም አቀፍ የፍርድ ቤት ውሳኔን ባለመቀበል ብቻ ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማትችል አንስተው የካሳ ክፍያው እስከሚከፈላቸው ድረስ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የሩሲያ ሀብቶችን ማደናቀፋችንን እንቀጥላለን ብለዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። ይሁን እንጂ ሩሲያ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እውቅና እንደማትሰጠው አስታውቃለች።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሩሲያ ባለስልጣናት የኖርዌይን እርምጃ “የባህር ላይ ዘረፋ” እና “ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ፖለቲካዊ ውሳኔ” ሲሉ ያወገዙት ሲሆን ሩሲያ ውሳኔውን በህግ እንደምትታገል አስታውቃለች።
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ

6
2
1September 4, 2026 3.2K