የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን የቀጠለውን ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል እንዳለው ገለጹ
ዓርብ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
ፑቲን ይህንን የተናገሩት በሩሲያዋ ቭላዲቮስቶክ በተካሄደው የምስራቃዊ ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ሲሆን የጦርነቱ ዋና ተሳታፊዎች ሩሲያና ዩክሬን በመጀመሪያ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
“ለሰላም ዕድል አለ? በእኔ እምነት አዎ፣ ዕድል አለ” ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።
በዩክሬን ጉዳይ ሩሲያና አሜሪካ ግንኙነታቸውን እንደቀጠሉ የገለጹት ፑቲን፣ ግንኙነቱ የስለላ ቻናሎችን ጨምሮ በተለያዩ መስመሮች እየተካሄደ ነው ብለዋል።
ከአሜሪካ ጋር ያለው ግንኙነት መሻሻል በሁለቱም ወገኖች ጥረት ላይ እንደሚመሰረት የተናገሩት ፑቲን፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገንቢ ለሆነ ትብብር ፍላጎት አላቸው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
ፑቲን በበኩላቸው በሲቪል መርከቦች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና የጥቃት ዛቻዎች የሰላም ድርድርን ያወሳስባሉ ያሉ ሲሆን የሲቪል መርከቦች መያዝ፣ በንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸም እና በሲቪል አውሮፕላኖች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚደረጉ ዛቻዎችን “የመንግሥት ሽብርተኝነት” በማለት ገልጸዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ፑቲን ይህን ከማለታቸው ቀደም ብሎ በሩሲያ አየር ክልል አየር መንገዶች እንዳይበሩ አስጠንቅቀው ነበር።
እንደ ፑቲን ገለጻ ከሆነ የዩክሬን ደጋፊ የሆኑ ምዕራባዊ አጋሮች እንዲህ ያሉ ድርጊቶችን በመቃወም እርምጃ ካልወሰዱ የዓለም አቀፍ ሽብርተኝነት ተባባሪዎች ሊባሉ ይችላሉ ብለዋል ።
ፑቲን ሩሲያ የአየር መከላከያ ሥርዓቷን በፍጥነት እያሻሻለች መሆኑን ጠቁመው፣ ከሁለት ቀናት በፊት በሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች ሁሉ መመከታቸውን ተናግረዋል።
በሩሲያ አዲስ የጦር ሰራዊት ቅጥር ሊካሄድ ነው የሚሉ ዘገባዎችን ውድቅ ያደርጉት ፑቲን “በአሁኑ ጊዜ የጦር ሰራዊት ቅጥር እንዲካሄድ የሚያስገድድ ሁኔታ የለም” ሲሉ ገልጸዋል።
የጦር ሰራዊት ቅጥር ይካሄዳል የሚለው ወሬ በሩሲያ የስቴት ዱማ ማለትም የፓርላማ ምርጫን ለማወክ እየተሰራጨ ያለ መረጃ ነው ብለዋል ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሩሲያ ነጋዴዎች በቅርቡ በፈቃዳቸው በመቶ ቢሊዮን ሩብል የሚቆጠር ገንዘብ ለመንግሥት በጀት ማበርከታቸውን የገለጹ ሲሆን ይህም ለእሳቸው “ፍጹም ያልተጠበቀ ነገር” እንደነበር ፑቲን መናገራቸውን አናዶሉ ዘግቧል ።
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ

3September 4, 2026 1.9K 1