የኬንያ የጤና ባለሙያዎች ከደሞወዝና የሥራ ሁኔታን በተመለከተ የጀመሩት አድማ 38ኛ ቀን ማስቆጠሩ ተገለፀ… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
የኬንያ የጤና ባለሙያዎች  ከደሞወዝና የሥራ ሁኔታን በተመለከተ የጀመሩት አድማ 38ኛ ቀን ማስቆጠሩ ተገለፀ
 
 ዓርብ፣ ነሐሴ 29  ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)

በኬንያ  የሚገኙ  የጤና ባለሙያዎች  ከደመወዝና የሥራ ምቹ ሁኔታን በተመለከተ የጀመሩት  የሥራ ማቆም  አድማ 38ተኛ ቀን ማስቆጠሩ ተገለፀ ፡፡

በትላንትናዉ ዕለት ነጭ ገዋን የለበሱ እና መፈክር የያዙ በርካታ ነርሶች በናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ መታየታቸዉ ተሰምቷል፡
 
የተቃዉሞ ሰልፉ የሀገሪቱ  መንግስት  ረዥም ጊዜ   ያስቆጠሩ  ከደመወዝና ከሥራ ቦታ ሁኔታ ጋር  የሚገኛኙ   ቅሬታዎችን ለመፍታት አለመቻሉን  ለማዉገዝ ያለመ  እንደሆነ ተነግሯል።
 
የኬንያ ብሔራዊ ነርሶች ማኅበር ዋና ጸሐፊ ሴህ ፓናይኮ እ.አ.አ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ  የደመወዝ እና ክፍያ ኮሚሽንና በገዥዎች ምክር ቤት መካከል  ጉዳዮን የማንሳትና የመጣል ሁኔታ ሲታይ  ቆይቷል  ብለዋል። 

አክለዉም በዕለቱ ደመወዝ እና ሌሎች ክፍያ የሚጽምላቸው ኮሚሽን በመጎብኘት በኮሚሽኑ በኩል  ያለዉን አቋም እንዲነግሯቸው እና ድርድር በማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ ተቋሙ ምንም አይነት ተቃውሞ እንደሌለዉ ለማመላከት ደብዳቤ እንደሰጧቸው ለመጠየቅ  እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ  ከጀመረዉ የሥራ ማቆም አድማ  በኋላ የኬንያ ብሔራዊ ነርሶች ማኅበር ፕሬዚዳንት በታካሚዎች ላይ  ስለሚያመጣዉ ተጽዕኖ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
 
ፕሬዚዳንቱ  እንዳሉት ከሆነ የነርሶች የሥራ ማቆም አድማ 38ኛ ቀኑን እንዳስቆጠረ ገልጸው በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግሥት የጤና ተቋማት በዚህ የሥራ ማቆም አድማ  ሳቢያ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረሰባቸው እንደሆነ አንስተዋል። 
አክለዉም እንዴ እሳቸው እንደ አንድ የጤና ባለሙያዎች ባልደረባ ጉዳዩ  አሳሳቢ ነው ያሉት ሲሆን ይህም “ቀጣይነት ያለው   የአገልግሎት መስተጓጎል  ታካሚዎች ላይ እና የጤና አጠባበቅ ሥርዓቱ  ላይ ጉዳት እያስከተለ ነው” ብለዋል፡፡
 
በሌላ በኩል ደግሞ የክሊኒክ መኮንኖች ማኅበራት ዋና ጸሐፊ  ጆሴፍ ቼቢ አስቸኳይ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት  አሳስበዋል፡፡
 
“በእናቶቻችን እና በሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች መካከል መከላከል  የሚቻሉ  ሞቶች እየጨመሩ መምጣታቸውን አሁን እያየን ነው።” ያሉ ሲሆን “መዘግየታችን ከቀጠልን ብዙ ተጨማሪ ኪሳራዎች ይደርሳሉ።  ስለዚህ የእኛ ጥሪ ለማኅበራቱ፣ ለኮሚሽኑና፣ ለሀገሪቱ ለመንግሥት፣ ለክልል መንግሥት እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ጠረጴዛ ተቀምጠው ጉዳዩን እንዲወያዩበት እና እንዲፈቱት ነው”  በማለት ገልጸዋል፡፡

በማኅበሩ እና በገዥዎች ምክር ቤት መካከል የተደረጉ ውይይቶች ውጤት አልባ ሆነው በመቆየታቸው ነርሶች ከሥራ ማቆም አድማው ጋር ተያይዘው ተቃውሟቸውን እንዲያጠናክሩ አድርጓቸዋል  ተብሏል።
 
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤4
September 4, 2026 2.9K