ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ ቅዳሜ፤ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

ቅዳሜ፤ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ)

የጉሙሩክ ኮሚሽን በአንድ ሳምንት ውስጥ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች  በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

ኮሚሽኑ ከነሐሴ 21 እስከ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አደረኩት ባለው ክትትል፣ 470.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የገቢ እና 81 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችን በድምሩ 551.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ እቃዎችን መያዝ መቻሉን አስታውቋል።

ከተያዙት እቃዎች መካከል ጨርቃጨርቅ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ መዋቢያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳትና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል።

በኮንትሮባንድ ቁጥጥሩ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ የጉምሩክ ቅርንጫፎች ቀዳሚ ሲሆኑ  ቅርንጫፎቹ በቅደም ተከተል 186 ሚሊዮን፣ 117 ሚሊዮን እና 116 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ እቃዎችን ይዘዋል።

እቃዎቹ በፍተሻ፣ በጥቆማ እና በበረራ ላይ በተደረገ ክትትል የተያዙ ሲሆን፣ 26 ተጠርጣሪዎችና 10 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ መግለፁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች ።

ጉምሩክ ኮሚሽን ኮንትሮባንድና ሕገወጥ ንግድን ለመከላከል ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላትና ከሕብረተሰቡ ጋር በመተባበር የሚሠራ ሲሆን፣ ሕገወጥ ንግድን ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤5👏2
September 5, 2026 2.7K 1 2