በአማራ ክልል በሚፈፀሙ ግፎች ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ራሳቸውን የሚያጠፉ ጎልማሳዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናገሩ ‼️ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በአገዛዙ የጭካኔ ድርጊት እና ውድመት ምክንያት ተስፋ በማጣት ራሳቸውን የሚያጠፉ ጎልማሳ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎችና የህክምና ባለሙያዎች ተናገሩ። ራስን ለማጥፋት ምክንያቶቹ የአዕመሮ ህመምና ቅፅበታዊ አደጋዎች የሚፈጥሩት ተስፋ የማጣት አጋጣሚዎች መሆናቸው ተገልጧል። በባሕር ዳር ከተማ ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ 156 ነዋሪዎች ከራስ ማጥፋት ጋር በተያያዘ ወደ ህክምና እንደመጡ አንድ የህክምና ባለሙያ ተናግረዋል። በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ጓዴ ከአዲሱ ዓመት መግቢያ ጀምሮ ራስን የማጥፋት አደጋ ጉዳተኞች ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸውን ገልጸውልናል። ከታካሚዎቹ መካክልም ብዙዎቹ ከተጎዱ፣ ህይወታቸውን ካጡ በኋላ ወደ ተቋሙ በመድረሳቸው ሕይወታቸው ያለፈ መኖሩን አመልክተዋል። ክልሉ በፋሽስቱ አገዛዝ ወረራ ስር ከወደቀበት ያለፉት 2 ዐመታት ውስጥ በጨካኝ የአገዛዙ ወታደሮች ከሚጨፈጨፉት ባልተናነሰ በየቀበሌው መድሃኒት እና ህክምና በማጣት፣ እንዲሁም አገዛዙ በሚፈፅማቸው ውድመቶች እና ጭካኒያዊ ግድያዎች፣ አሻጥራዊ እገታዎች ምክንያት ተስፋ ያጡ እናቶች እና ጎልማሳዎች ራሳቸውን እያጠፉ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች አጋልጠዋል። ዶቼቬሌ(DW) #የቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join አድርጉ። #ድል፣ ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 መጋቢት 25/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ⚖🗣📢 @Moamediamoresh https://t.me/Moamediamores
በአማራ ክልል በሚፈፀሙ ግፎች ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ራሳቸውን የሚያጠፉ ጎልማሳዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን… — ATAYE MEDIA TUBE — TG.ME
April 3, 2025 676