በኩረ ነገራችን፣ #አምሓራዊ አንድነታችንን ማፅናት ይሁን‼️ ህልውናዊ አደጋ፣ በኩረ አመክንዮ ሆኖት… — ATAYE MEDIA TUBE — TG.ME

በኩረ ነገራችን፣ #አምሓራዊ አንድነታችንን ማፅናት ይሁን‼️ ህልውናዊ አደጋ፣ በኩረ አመክንዮ ሆኖት "#አምሓራዊነት" ያላሰባሰበው ሁሉ… ስናዳሪ ነው…! አምሓራዊ፣ የህልውና አደጋህ የጋራ እጣ ፋንታ ሆኖ አጋምዶ፣ አዋድዶ…አንድ ሊያደውርግህ ካልቻለ… ቀጠናዊ የህልውና እጣ ፋንታ አንድ ፍኖት፣ አንድ ጋርዮሻዊ እጣ ፋንታ እና ግንባር ሊቀይስልህ አይችልም። ከመሰለህም… የስህተት፣ ወደ ዳግማዊ የቁማር ወጥመድ እና ስናዳሪነት እየገሰገስክ ነው። ህልውናዊ አደጋ አብሮ ለማሰለፍ በኩር አመክንዮ ከሆነ… #አምሓራዊነት ከቅድመ መስፈርት በፊት ሊያሰባስብህ በቻለ… ቀድሞ ነገር፣ ከዐምሓራ በቀር ቀጠናዊ የህልውና አደጋ የተደቀነበት ህዝብ የለም። ሌላው ቡድን "ህልውናዊ አደጋን" ተጨባጭ ያልሆነ ለፕሮፖጋንዳ የሚጠቀመው ነው። ህወሓት ህልውናዊ አደጋ ቢገጥማት እንጅ፣ የትግራይ ህዝብ የህልውና አደጋ የለበትም። አምሓራ ያጋጠመው ግን፣ አምሓራዊ የህልውና አደጋ ነው። ሆኖም፣ ከይቅርታ ወዲህ፣ ከህዝባዊ አንድነት ቀድሞ…የአምሓራ ህልውናዊ አደጋ ምንጭ፣ የጥላቻ ኬማስትሪ ቀማሚ እና ኤክስፐርት፣ መምህር እና ተማሪ ከሆኑት፣ በታሪክ እጃቸውን በአምሓራ ደም ካጨቀዩ ቡድኖች ጋር አብሮ ለመስራት… ለመሰለፍም ጋርዮሻዊ የህውና አደጋ አጣምሮ ግንባር ለመፍጠር ወኔ ከሰጠን ዘንዳ… አምሓራ ከሆነው፣ በጋራ እጣ ፋንታ እና ደም (poletical fate and blood) ተጋምዶህ ነገር ግን በጋራ ለመስራትም፣ አንድ ድርጅት ስርም ለመሰባሰብ የሚያስችል ወኔ ከተሰለብክ…ችግር አለ። አንተ አንተ አይደለኽም ማለት ነው። ታክቲካዊ ይሁን ስትራቴጅካል በሆነው ፍኖት… ከወያኔ ከሻብያ ከኦነግ ጋር አብሮ ለመስራት፣ ግንባር ለመፍጠር ተደፋፋሪ ዝግጁም ስነ ልቦና ኖሮህ ሳለ… እንዳንተ ደመ አምሓራዊ ህልውናውን ለማስከበር ጫካ ከወጣ አምሓራ ወንድምህ ጋር አንድ መስመር መያዝ ካቃተኽ? መመርመር አለብህ! የአምሓራ ህዝብ ጥቅሞችን ሸራርፎ፣ ቆራርሶ በመሸጥ… ከዐገዛዙም ይሁን ከሌሎች ጋር በጀርባ ቁማር የሚጫዎቱ ቡድኖች እና ግለሰቦች ይጠነቀቁ! የአምሓራ የመጀመሪያ ረድፈኛ ጠላት፣ ጠላቶቹን ተሸክሞ ለዙፋን የሚያበቃ ስናዳሪ ብዐዴናዊነት ነው። አምሓራዊ ሆኖ፣ የትኛውንም ቀጠናዊ አንድነት፣ ጋርዮሻዊ ህብረት፣ ዘላቂ እና ጊዚያዊ ጥምረትን በጥበብ ለመጫዎት የሚሻ ቡድንን መለኪያችን ሚዛን አንድ ነው። እርሱም፦ ለአምሓራዊ አንድነቱ ባለው ባለፋይዳ ቁርጠኝነት ነው። ዱር ቤቴ ያለን ወንድሙ እያጥላላ፣ እየፈረጀ… ከወያኔ እና ሻዕቢያ ጋር አንሶላ ለመጋፈፍ አልጋ ሲያነጥፍ ከተገኘ፣ ችግር አለ። ሩቅ ታሳቢ ለሆነ አላማ ጋርዮሽ ለመፍጠር ቢቻል እንኳ…አምሓራዊ ጥንካሬን ከማዎጃችን ማግስት ይሆን ዘንድ ጉዳዩ፣ የይደር ታሳቢ ነው። ፖለቲካዊ ጥበብ፣ ዲፕሎማሲያዊ ሳይንስ፣ የፕሮፖጋንዴ ስልትህ ዋጋቸውን የምንመዝነው፣ ለዐምሓራ ህዝብ አንድነት እና ትንትን ጥቅሞች ባላቸው ዋጋ ነው። በስልት ሆነ ተብሎ የተከፋፈለ ደካማ አምሓራዊ ሰልፍ ይዞ… ከገነገኑ ባለ ልምድ የቀደሙ ጠላቶቻችን ጋር ጊዜያዊ ማዕደ ፖለቲካ፣ ሰልፈ ጦር ላይ በስሜት መራዠት ድንበራ መሰለፍ ለትርፍ አይሆንም። #አምሓራዊ ሰልፋችንን አሸናፊ ለማድረግ እጅግ ጥንቃቄ እና ከዐውዳዊ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ንቃት የሚቀዳ ጥበበ ትልም ያስፈልጋል። በኩረ ነገራችን፣ አምሓራዊ አንድነታችን ማፅናት ይሁን! ከዐምሓራዊ አንድነታችን የምናስቀድመው የጓሮ ተናጠላዊ ውሽምነት… ዝሙት፣ የአምሓራ ህዝብ ላይም ክህደት መፈፀም ነው! ከራስ አንድነት ጥንካሬ በፊት ያለ ንጡል ግንኙነት… ብትን የሚሸቀጥ፣ ከአምሓራዊ አላማ የተዛነፈ መስመር ያስይዛል! እደግመዋለሁ…! በኩረ ነገራችን፣ አምሓራዊ አንድነታችንን ማፅናት ይሁን! #ሌላው፣ እዳው ገብስ ነው! @Hiruy Amhara #የቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join አድርጉ። #ድል፣ ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 መጋቢት 24/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ⚖🗣📢 @Moamediamoresh

April 2, 2025 342