ሰበር የድል ዜና በዘመቻ አንድነት !! ስድስተኛ ቀኑን በያዘው ዘመቻ አንድነት በአማራ ፋኖ በጎጃም ሶስተኛ ጎጃም አገው ምድር ክፍለጦር ታሪካዊ ድምሰሳ አደረገ። የአፋጎ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ዛሬ አቸፈር ምድር ላይ ታሪክ ሰርቷል። ከንጋቱ 12:00 ስዓት 4:00 ስዓት ድረስ በቆየዉ ከፍተኛ አዉደ ዉጊያ መንትዮቹ የቢትዎደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድና የአቤ ጉበኛ ብርጌድ በጥምር ጠላትን ዶጋ አመድ የአደረጉት ሲሆን ክ/ ጦሩ ለሁለቱ ብርጌድ በክፍለ ጦሩ አመራሮች ወታደራዊ እና ፓለቲካዊ ስልጠና ሲሰጥ ከሰነበተ በሆላ በዛሬዉ ዕለት ሊበን ከተማን በመቆጣጠር ጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሷል። በዚህም :- 1/ 46 በላይ የጠላት ሃይል የተሸኘ ሲሆን 2/ 29 የቆሰለ 3/ 24 ክላሽ የማረከ 4/ 2 ፓትሮል የተቃጠለ 5/ 2 ሞተር የተቃጠለ 6/ 2 ኮምፒተር የባንዳዉ መገልገያ የነበረ የተማረከ ሲሆን ይህንን ሃይል ሽፋን ለመስጠት ከዝብህስት የተነሳ ሃይልን አሹዳ ላይ ፈንጅ በመጥመድ ጉዳት የደረሰ ሲሆን 7/ 1 ዙ_23 ከጥቅም ዉጭ የሆነ 8/ 1 ፓትሮል የነደደ ሲሆን 9/ ለጊዚየዉ ማዕረጉን ያልታወቀ በእጀባ የነበረ አመራር ከነ ፓትሮሉ የተደመሰሰ ሲሆን 10/ 11 የጠላት ሃይል ወደ ላይኛዉ የተሸኘ 11/ 10 ቁስለኛ ሁኗል 12/ ከጭንባ ያለዉ ጠላት ወደ ሊበን እንቅስቃሴ ሲጀምር የባህር ዳር ብርጌድ ጊዮን ሻለቃ በዲሽቃ ጭንባ ላይ ያለዉን የጠላት ካንፕ የደበደበ ሲሆን 1 ፓትሮል ከጥቅም ዉጭ ሁኗል። ዘመቻ አንድነት ይቀጥላል ። (የአማራ ፋኖ በጎጃም)
1