ዘመቻ አንድነት የጎንደር ግንባር ፭ኛ ቀን ረፋድ 4:00 ሰዓት መረጃ 5ኛ ቀኑን በያዘው ዘመቻ አንድነት የጎንደር ግንባር ውጊያ ድሎች 🔸በጎንደር ከተማ አስተዳደር ጠዳ ክ/ከተማ ዘልቆ በመግባት ብርቱ ውጊያ ያደረገው የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ለ26 ሰዓታት አድማሱን እያሰፋና እያጠበበ ቀጥሎ አምሽቷል። በጎንደር ከተማ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫና ደቡባዊ አቅጣጫ የቀጠለው አውደ ውጊያ በጠዳ ከበባ ስር የነበረውን ጠላት ለመታደግ ተልዕኮ የተሰጠው የጠላት ሀይል ከጎንደር ከተማ ማረሚያ ቤት አቅጣጫ በመነሳት አምቦበር ከፍታን ከጀርባ ለመቁረጥ እየገሰገሰ መሆኑን በመረዳት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ለቆረጣ የመጣውን ጠላት በመቁረጥ እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት በሚገባ ተገርፎ ሙትና ቁስለኛውን አዝረክርኮ የተረፈው እግሬ አውጭኝ ብሎ ጎንደር ገብቷል። የተደመሰሰ 07 የቆሰለ 11 ሁኖ ተጠናቋል። 🔸 በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ ምስራቃዊ አቅጣጫ ስሆር እና ውግሎ በተሰኙ ልዩ ቦታዎች የነበረው ውጊያ ቁጥሩ ለጊዜው ያልታወቀ ጠላት ሙትና ቁስለና ሁኗል። 🔸 በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ አምባጊዎርጊስ ከተማ ዘልቆ በመግባት ጥቃት ማድረስ የቻለው የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ምስጋናው አጣኔ ብርጌድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ በጠላት ላይ ያደረሰ ሲሆን የተረጋገጠ መረጃ ሲደርሰን እናሳውቃለን። 🔸 በምዕራብ በለሳ ወረዳ 13 የአገዛዙ ሚሊሻዎች በዘመቻ አንድነት ወታደራዊ ጫና ምክንያት እጃቸውን ለአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሰራዊት በመስጠት ጠላትን መልሰው ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ዘመቻ አንድነት ይቀጥላል... ህልውናችን በተባበአ ክንዳች መጋቢት 14/2017 ዓም ጎንደር/አማራ/ ኢትዮጵያ
1