በእርጋታየሚነበብ (መ-ገንዘብ 2 ላይ ሜታዳታ ለገባው ሰው ቀላል ነው) ============== በቀጣይ 10… — Hasen Injamo — TG.ME

በእርጋታየሚነበብ
(-ገንዘብ 2 ላይ ሜታዳታ ለገባው ሰው ቀላል ነው)
==============
በቀጣይ 10 ዓመት የቢዝነስ እና የትምህርት ሁኔታ ምን ይመስላል ብለን ብንጠይቅ የሚነግረን ሰው አናገኝም:: ለመገመት በሚያስቸግር ረቂቅ አኗኗር ውስጥ እየገባን ነው:: ስለፊያት እያስረዳሁ ሜታዳታ ወረረን:: አሁን ዘመኑ የሜታዳታ ነበር ግን ፈጥነን ወደ ፕሮግራመብል ገንዘብ እየገባን ነው:: በዚህ በቅርብ ዓመታት ኢንፍሌሽን ታሪክ ይሆናል:: ምክንያቱም:- ስፔኩሌሽን Ai እና በንግድ ባንክ CBDC እና ማዕከላዊ ባንክ CBDC አማካይነት ይጠፋል:: ትርጉማቸው በጣም አሳሳች ስለሆኑ ረጋ ብሎ ማንበብ ይፈልጋል:: -ገንዘብ 2 እና 3 ላይ በደንብ አሉ:: በቀጣይ ምን ይሆናል?

1) በተፈጥሮ ሃብት የሚደገፉ ተንቀሳቃሽ የፋይናንስ መሣሪያዎች (Dynamic Real-Asset Liquidity - DRALs) ይመጣሉ:: ይህም የምድር ለምነትን፣ የኃይል አቅርቦትን፣ ውድ ማዕድናትንና መሠረተ-ልማቶችን በዲጂታል መልክ በመወከል ወዲያውኑ ወደሚዘዋወር የፋይናንስ አቅም ይለውጣቸዋል።

2) በኃይልና በምርት የተመዘነ የልውውጥ መለኪያ (Energy-Weighted Clearing Unit) ሌላው ነው:: ይህም ገንዘብ በሳንቲም ከመለካት ወደ ጁል እና ኪሎዋት ሊወስደን ይችላል:: ኢንደስትሪው ወይም ሀገሩ ስንት ኪሎዋት ተጠቀመ? ስንት ኸርዝ ወሬ አደመጠ? ወደማለት ይኬዳል::

3) የቬክተር ሜታዳታ የፋይናንስ ማጽጃ ሞተር (Vectorized Metadata Clearing Engine):-

-> ጽንሰ-ሀሳብ፡ በባህላዊ ሥርዓት ገንዘብ "ደን^ቆሮ ገንዘብ" (Dumb Money) ነው:: ማለትም ምንም ዓይነት መረጃ የሌለው ቁጥር ብቻ ነው። በ AI ሥርዓት ግን እያንዳንዱ የፋይናንስ ክፍል የራሱ ትርጉም ያለው መረጃ (Semantic Metadata) ይይዛል።

-> የ AI ሚና፡ AI የእያንዳንዱን ሃብት መገኛ፣ የምርት ጥራት፣ የስርጭት ርቀት እና የባለቤትነት ታሪክ ይከታተላል። አንድ የንግድ ድርጅት ክፍያ ሲፈጽም ቁጥር ብቻ ሳይሆን የሃብቱን እውነተኛ አካላዊ ምንጭ የሚያረጋግጥ የተጠበቀ ዲጂታል መረጃ (Vector) አብሮ ያስኬዳል።

4) ራስ-ሰር ገበያ አስተካካይ (Autonomous Equilibrium Market Makers - AEMM)

-> ጽንሰ-ሀሳብ፡ የባህላዊ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ ምጣኔ ውሳኔዎች በሰዎች ፍላጎትና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ የተወሰኑ በመሆናቸው ለቀጣይ ቀውስ ይዳርጋሉ።

-> የ AI ሚና፡ በ AI የሚመራው ማዕከላዊ የማጽጃ ኢንጂን እንደ ድንገተኛ አደጋ መከላከያ ይሠራል:: የማሽን ትምህርት (Machine Learning) ሞዴሎችን በመጠቀም የገንዘብ ዝውውር ፍጥነትንና የካፒታል ጥቆማዎችን በቅጽበት በማስተካከል የገበያ አረፋዎችን (Speculative Bubbles) እና የገንዘብ እጥረትን አስቀድሞ ይከላከላል። ስፔኩሌሽን ከሌለ የገንዘብ አረፋ አይኖርም:: ይህም ግሽበትን ለመከላከል በጣም ይረዳል::

ሆኖም ግን መንግሥታት ይፈልጉታል? ወደ ወረቀት ገንዘብ እንመለስ ሊሉ ይችላሉ:: ግን too late.
❤6
September 5, 2026 1.6K 2