Goqa-ጎቃ (Ethio-news): post #15536 — TG.ME

በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ የጋራ መኖርያዎች የተሰማው ንዝረት መነሻው ምን ነበር??

⚡️ትላንትና ከምሽቱ 4 ሰዓት ቡሃላ የመሬት ንዝረት እንደተሰማቸው የገለፁ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነበሩ። ከዚህ ቀደም አንዳየነው አንዲህ አይንት ንዝረቶች የሚከሰቱት በአንድ የሀገሪቷ ክፍል ውስጥ ተሰሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲፈጠር ሲሆን የትላንትናውን ንዝረት ያስከተለው በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ የተከሰተ በሬክተር ስኬል 4.6 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ነዉ።

⚡️በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳ እና አካባቢው ከታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለችው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እየተፈጠሩ እንደሆነ የገለፀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ፣ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ይህኛው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የፈንታሌ ተራራን መሰንጠቅ እና መደርመስ ማስከተሉን ገልፆል።

💥በሬክተር ስኬል መሰረት ከ 4.0 አስከ 4.9 ያሉት የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች መለስተኛ ሲባሉ በአካባቢው ላለ ሁላ የሚሰሙ አና ትናንሽ አቃዎችን የሚሰብሩ ቢሆንም ከተፈጠረበት አካባቢ አንፃር ለተራራው መደርመስ ምክንያት ሆኗል።

©Tikvah
#መሬት_መንቀጥቀጥ #ፈንታሌ_ተራራ #ኢትዮጵያ

Join Us
https://t.me/+6HHF7MBj0VUyMjVk
🤯3🙏1
December 24, 2024 2.1K