CHRISTIAN INSIGHT: post #264 — TG.ME

ከገበያው ውጡ

ያላችሁበት ገበያ ምን የሚሸጥበት እንደሆነ ስለማታውቁ አብዛኞቻችሁ ያላችሁበት ገበያ ለእናንተ የሚመጥን አይደለም።

አያችሁ ይሁዳ መገኘት በሌለበት ገበያ ተገኝቶ ነው ክርስቶስን ሽጦ የወጣው። መሸጡ የማይገባ እንደሆነ ተረድቶ ለመመለስ እና ክርስቶስን ለማስመለስ ቢመለስም እሺ ብለው አልመለሱለትም ነበር።

እናንተስ የትኛው ገበያ ውስጥ ነው ያላችሁት ? ምናልባት ክርስቶስ የሚሸጥበት ገበያ ቢሆንስ ? አሁን አንድ ነገር አድርጉ ያላችሁበትን ገበያ ተመልከቱ። ምድር ክርስቶስን ለሚሸጥ ትልቅ ጥቅምና ቦታ ትሰጣለች። ምናልባት የተሰጠን ትልቅ ቦታ የተሰጠን ክርስቶስን በዚያ ቦታ ላይ አስጥሎን ቢሆንስ ?

ክርስቶስ የሚሸጥበት ገበያ በተለምዶ የሚሞቅና የሚደራ ነው። ለመሳተፍም መነሳሳትን ይፈጥራል።

ገበያው ምናልባት የምንሰራው ስራ ፡ የምንውላቸው ሰዎች ፡ የምንገባበት ቤት ፡ የምንውልበት ቦታ ፡ የምንወዳቸው ሰዎች even ቤተሰቦቻችን ሊሆኑ ይችላሉና በደንብ ተመልከቱአቸው።

ክርስቶስ የሚሸጥበት ገበያ መገኘትና በግብይቱ መሳተፍ የሚቀበሩበትን ጉድጓድ እንደ መቆፈር ነው።


@Christian_Insight
@Christian_Insight
❤4🥰2👍1
November 17, 2025 187