CHRISTIAN INSIGHT: post #259 — TG.ME

ልካችንን እንወቅ

በእጃቸው እንዲገባ የሚፈልጉትን ነገር ከአላማቸው አንፃር የቃኙና ልካቸውን የሚያውቁ ሰዎች በዚህ ምድር ላይ ያላቸውን ዓላማና ግብ በሚገባ አውቀውና አገናዝበው ለዚያ አላማቸውም ምን እንደሚያስፈልጋቸው ለይተው የተደላደሉ የተመቻቹ ሰዎች ናቸው።

ልክህን ስታውቅ ተለክተህ እንደተፋለህ ልብስ ሁሉ አስተሳሰብህም ሆነ ምኞትህ በአንተ አቅም መመጠኑን ያሳይሃል።

ልክህን እወቅ ሲባል ቀላል ንግግር አይደለም። በልክህ መኖር፣ በልክህ መመላለስ ፣ በልክህ ማሰብ፣ በልክህ መብላት፣ በልክህ ማውራት የመጠንህንና የአቅምህን ልኬት ያሳይሃል።

በልክህ ባሰብክ ቁጥር ጭንቀትን መቀነስ ትችላለህ ከአቅምህ በላይ ባማይመለከትህ፣ በማያገባህ  ነገረ ያሰብክ እንደሆነ ግን ማሰቡን ትተህ ወደ ጭንቀት ጉድጓድ ሰተት ብለህ ገባህ ማለት ነው።

ሁሉም ነገር በልክና በአቅም መጠን ሲሆን ውብ ነው፤ ደስም ይላል። ልክህ የህይወትህ ጠዓም መለኪያ ነው። በልክህ እየኖሮክ እንደሆነ የህይወት መልካም ገፀበረከት ያለማንም ከልካይነት ወደ ቤትህ ይገባል። ስለዚህ በልክህ መኖርን አዘውትር፣ በልክህ ማሰቡንም እንዲሁ። በልክህ አውራ ፣ በልክህ እየወጣህ ግባ። ያለ አቅምህ እየተንጠራራህ እንዳትሰበር ተጠንቀቅ።😎😎

love you .!

@Christian_Insight
@Christian_Insight
❤2👍1🔥1
September 16, 2025 181