CHRISTIAN INSIGHT: post #255 — TG.ME

ቶሎ ቶሎ ውለዱ

🍀 ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው። ለመሳቅ ፡ ለማልቀስ ፡ ለመውጣት ፡ ለመግባት እንዲሁም ለመውለድም ጊዜ አለው።

🍀 አንድ ነገር ጊዜ አለው ማለት ያንን ነገር ለማድረግ ምርጡ ጊዜ እሱ ነው ማለት ሲሆን ፡ ያ ጊዜ ሳይመጣም ሆነ ካለፈ በኋላ ያንን ነገር ማድረግ አንችልም።

🍀 ለምሳሌ ለመውለድ ጊዜ አለው ከሆነ እድሜ በላይ እና ከሆነ እድሜ በታች ነው መውለድ የሚቻለው። ከዚያ የጊዜ ማዕቀፍ ውጪ መውለድ አይቻለም።

🍀 በህይወት ላይም ጊዜ የሚባል ነገር አለ። ከእናት ማህፀን የሚወለደውን ልጅ ራዕይ ወይም አላማ ነው እንበለውና አጠር ያለ ነገር ልበላችሁ። የወጣትነት እድሜ ራዕይና አላማችንን መውለጃ ምርጡ ጊዜ ነው። እሄንን ጊዜ ተጠቅመን በውስጣችን የሚመላለሰውን ራዕይ መውለድ አለብን።

🍀 ይህ ባይሆን ግን መውለድ ፈልገን እንኳን መውለድ የማንችልበት ጊዜ ይመጣል። በተወለዱ ራዕዮች ስንቀና እንኖራለን። ስለዚህ ባላችሁ በዚህ ጊዜ ቶሎ ቶሎ ውለዱና ተገላገሉ። እኛም እንኳን ጌታ ረዳችሁ ለማለት ቸኩለናል።

የተወደዳችሁ ናችሁ

@Christian_Insight
@Christian_Insight
❤2👍1🔥1🥰1
September 2, 2025 163