CHRISTIAN INSIGHT: post #249 — TG.ME

"ያጠለቅነው ጫማ ባዶ እግራችንን፣ የለበስነው ልብስ ዕራቁት መወለዳችንን ካስረሳን ሞኝ ነን። በባዶነት ጀምረን በባዶነት በምንጨርስባት ዓለም ሁሉ የእኔ ካልሆነ ብለን አንታክት። በድብቅ እየወደቅን በገሀድ የወደቁት ላይ አንዘባበት። ትምህርታችን ያልተማሩትን ካልረዳ አለማወቅ ነው። የእኛን ትምህርት ዋጋ ያለው ያደረገው ያልተማሩት ናቸው። ጨለማን የማያስወግድ ብርሃን ራሱ ጨለማ ነው። ፍላጎታችንን ባለማወቅ የሰውን ድንበር አንግፋ። በክብር ለመኖር ልክን ማወቅ መሠረት ነው። ሐሰትን ከፈጠራት ያሰራጫት የከፋ ነውና የማናውቀውንም የምናውቀውንም ከመናገራችን በፊት እናስተውል።"

@Christian_Insight
@Christian_Insight
❤2🔥1🥰1
August 24, 2025 156