Addis Intelligence: post #15235 — TG.ME

🔍 Alibaba በኮምፒውተር ላይ በቀጥታ (Locally) የሚሰሩ አዳዲስ የ-Qwen3.8 ክፍት ሞዴሎችን ይፋ አደረገ

Alibaba አዲሱን 27 ቢሊዮን Parameters ያለውን Qwen3.8-27B ጨምሮ ሁለት የ-Qwen3.8 ሞዴሎችን Model Weights በክፍት ምንጭ (Open Weights) ለቋል። Qwen3.8-27B በግል ኮምፒውተሮች ላይ በቀላሉ እንዲጫን የተዘጋጀ ሲሆን ጽሑፍን እና ምስልን (Multimodal) የሚደግፍ ከመሆኑም በላይ እስከ 262,000 Tokens (እስከ 1 ሚሊዮን Tokens የማስፋት እድል ያለው) የ-Context Window አቅም አለው።

• Qwen3.8-27B በኮምፒውተር ላይ በቀጥታ የሚሰራ የታመቀ (Compact) ሞዴል ቢሆንም በተለይ በፕሮግራሚንግ እና በቢሮ ስራዎች የቀድሞውን Qwen3.7-Plus በብቃት ይበልጣል

• የሞዴሎቹ Weights በ-Apache 2.0 ፈቃድ ስር የተለቀቁ በመሆናቸው ለንግድ (Commercial projects) ስራዎች በነጻ መጠቀም ይቻላል

• በተጨማሪም Alibaba ለከባድ የሰርቨር ስራዎች (Heavy server workloads) የሚሆን 2.4 ትሪሊዮን Parameters ያለው ግዙፍ Qwen3.8-2.4T-A95B ሞዴል ይፋ አድርጓል

ይህ Alibaba ለአካባቢያዊ (Local) አጠቃቀም ከሚሆኑ ሞዴሎች ጀምሮ እስከ ግዙፍ የሰርቨር መዋቅሮች ድረስ ሰፊ አማራጭ እንዲያቀርብ ያስቻለው ሲሆን ለ-developers በነፃነት የሚጠቀሙባቸው ኃያላን መሳሪያዎችን አበርክቷል።

🤩 @AddisIntel
👍2
August 18, 2026 63