Addis Intelligence: post #15254 — TG.ME

የ-Palantir ዋና ስራ አስፈፃሚ ትችትን ተከትሎ OpenAI እና Anthropic የዳታ አያያዝ ፖሊሲያቸውን (Data Retention) አሻሻሉ የ-Palantir ዋና ስራ አስፈፃሚ አሌክስ ካርፕ (Alex Karp) የ-AI ላቦራቶሪዎች የንግድ ድርጅቶችን መረጃ (Enterprise Data) በመውሰድ የራሳቸውን ብልጫ (Alpha) ለመገንባት እና የደንበኞችን አእምሯዊ ንብረት (IP) ለመውሰድ ይሰራሉ በማለት ክስ ሰንዝረው ነበር። ይህንን ተከትሎ ሁለቱ ግዙፍ የ-AI ኩባንያዎች የኮርፖሬት ደንበኞችን እምነት ለማስጠበቅ አዳዲስ እርምጃዎችን ወስደዋል። 🔺 አሌክስ ካርፕ ኩባንያዎች የራሳቸውን መረጃ ለ-LLM ኩባንያዎች አሳልፈው እንዳይሰጡ በማስጠንቀቅ፣ የ-AI ኩባንያዎች የመረጃ ባለቤትነትን እና ግልፅነትን በድፍረት መመለስ እንዳለባቸው አሳስበዋል ✴️ OpenAI የደንበኞችን የግል መረጃ ሳያስቀምጡ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ብቻ ለመቆጣጠር የሚያስችል “Private Safety Processing” የተሰኘ አሰራር መሞከር ጀምሯል 🤶 Anthropic በበኩሉ የኮርፖሬት ደንበኞች የራሳቸውን መረጃ በ-Anthropic ሰርቨሮች ፋንታ በራሳቸው የ-Cloud መሰረተ ልማት (Own Infrastructure) ላይ እንዲያከማቹ እና እንዲቆጣጠሩ ፈቅዷል ይህ እርምጃ በ-AI ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልልቅ ኩባንያዎች የመረጃ ሉዓላዊነትን (AI Sovereignty) እና የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃን ያለ አንዳች ስጋት ማስከበር ወሳኝ የገበያ መወዳደሪያ እየሆነ መምጣቱን ያሳያል። 🤩 @AddisIntel

👍2
August 24, 2026 88