➡️GenBio AI የሰውን ልጅ ህዋስ (Human Cell) አጠቃላይ ባህሪ በዲጂታል መንገድ መምሰል የሚችል አዲስ የ-AI ሞዴል ይፋ አደረገ GenBio AI የተሰኘው የቴክኖሎጂ ተቋም DNA፣ RNA፣ ፕሮቲኖችን፣ የቁጥጥር ሰንሰለቶችን (Regulatory networks) እና አጠቃላይ የህዋስ ባህሪን በአንድ ላይ አቀናጅቶ መምሰል (Simulate) የሚችል AIDO Cell የተሰኘ አዲስ የ-AI ሲስተም ይፋ አድርጓል። ከዚህ ቀደም ለእያንዳንዱ ባዮሎጂካል ሂደት የተናጠል ሞዴሎችን ከመጠቀም ይልቅ AIDO Cell ሁሉንም ሂደቶች በአንድ ወጥ ሰንሰለት በማገናኘት ይሰራል ይህም በአንድ ጂን ላይ ለውጥ ሲደረግ ወይም አዲስ ኬሚካል ሲጨመር በህዋሱ ላይ የሚፈጠረውን ተከታታይ ተፅዕኖ እስከ አጠቃላይ ባህሪው ድረስ ያሳያል። 🖱️ AIDO Cell የህዋሱን የቀድሞ ሁኔታ (Cell state) የማስታወስ አቅም ስላለው ተከታታይ የሆኑ የህክምና ወይም የኬሚካል ለውጦችን እርስ በእርስ እያገናኙ በተጨባጭ ለመሞከር (Experimentation) ያመቻል 🖱️ ተመራማሪዎች ጥያቄ ጠይቀው መልስ ከማግኘት ባለፈ በዲጂታል ህዋሱ ላይ ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ የሆኑ የላብራቶሪ ሙከራዎችን እንዲያካሂዱ ያስችላል 🖱️ ሞዴሉ ገና በቅድመ-ዕይታ (Early preview) ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ወደፊት ሳይንቲስቶች ወደ ትክክለኛ የሰው ህዋስ ምርመራ ከመግባታቸው በፊት በቨርቹዋል ህዋስ ላይ ውስብስብ ሙከራዎችን እንዲያካሂዱ በር ይከፍታል ይህ አሰራር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለህክምና ምርምር ለመድኃኒት ቅመማ እና ለባዮሎጂካል ጥናቶች የሚወስደውን ጊዜና ወጪ በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ የሚያስችል ትልቅ የሳይንስ እመርታ ነው። 🤩 @AddisIntel
Addis Intelligence: post #15252 — TG.ME
August 23, 2026 79