የ-Google ኳንተም ቺፕ እጅግ ፈጣን ለሆነው ሱፐር ኮምፒውተር በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዓመታት የሚወስደውን ስሌት በ5 ደቂቃ ውስጥ ፈታየ-Google አዲሱ የኳንተም ቺፕ (Quantum chip) በዓለም ላይ እጅግ ፈጣን የሆነው ሱፐር ኮምፒውተር ለመፍታት በአስር ቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዓመታትን የሚፈጅበትን እጅግ ውስብስብ የሂሳብ ችግር በ5 ደቂቃ ውስጥ አጠናቋል። ይህ ውጤት በኳንተም ኮምፒውቲንግ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስደናቂ ከሚባሉ እመርታዎች መካከል አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።የ-Google ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰንዳር ፒቻይ (Sundar Pichai) እንደገለፁት ይህ ስኬት የኳንተም ስህተት ማረሚያ (Quantum error correction) በከፍተኛ ደረጃ ተግባራዊ መሆን መቻሉን ያረጋገጠ ነው። ፒቻይ አክለውም በተጨባጭ ለተግባራዊ አገልግሎት የሚውሉ አስተማማኝ የኳንተም ኮምፒውተሮች ከ5 እስከ 10 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ ዝግጁ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።ይህ ግስጋሴ ውስብስብ የሳይንስ ጥናቶች የቁሳቁስ ሳይንስን እና የህክምና መድኃኒት ቅመማን ሙሉ በሙሉ ሊቀይር የሚችል ግዙፍ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል። @AddisIntelt.me/Addisintel/15255Translate1August 24, 2026 57