በሳዑዲ ነሐሴ ላይ ብቻ ቢያንስ 60 ኢትዮጵያውያን ከዕፅ ጋር በተያያዙ ጥፋቶች መያዛቸውን ዘገባዎች አመለከቱ!
ከዕፅ ጋር በተያያዙ ጥፋቶች የሚፈረደቸባው ሰዎችን በሞት እየቀጣች ባለችው ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ፣ በነሐሴ ወር ብቻ ጫትን ጨምሮ የተለያዩ ዕፆችን በማጓጓዝ የተጠረጠሩ ቢያንስ 60 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዘገባዎች አመለከቱ።ትናንት ረቡዕ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም. ተጨማሪ 15 ኢትዮጵያውያን ከ290 ኪሎ ግራም ጫት ጋር መያዛቸው ተዘግቧል።
የሳዑዲ የድንበር ጥበቃ ጠቅላይ ዳይሬክቶሬት፣ 12ቱ ኢትዮጵያውን በቁጥጥር ስር የዋሉት ጃዛን እና አስሪ በተባሉት ግዛቶች ውስጥ በተካሄዱ ሦስት ዘመቻዎች እንደሆነ 'ሳውዲ ጋዜት' የተባለው አገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል።ሪያድ ግዛት ውስጥ ደግሞ የተከለከለ መድኃኒት ሲያስታዋውቁ ነበሩ የተባሉ ሌሎች ሦስት ኢትዮጵያውን መያዛቸውን የ'አልሪያድ' ዘገባ ያሳያል።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ሳዑዲ አረቢያ ከዕፅ ጋር በተያያዙ ክሶች ምክንያት በተፈረደባቸው ኢትዮያውያን ላይ ተከታታይ የሞት ቅጣት እየፈጸመች ባለበት ወቅት ነው።ባለፉት ሐምሌ እና ሰኔ ወራት በቀናት ልዩነት ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ቅጣቶች ተፈጻሚ ሆነዋል። ከጥር ወዲህ ቢያንስ 17 ኢትዮጵያውያን በሞት መቀጣታቸውን ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች 'ሂውማን ራይትስ ዎች' ሐምሌ ላይ አስታውቋል።
በአሁኑ ሰዓትም 200 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸው እስር ላይ እንደሚገኙ በስፍራው የሚገኙ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሳዑዲ ባለሥልጣናት ከዕፅ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች የጠረጠሯቸው ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ሥር ማዋል ቀጥለዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

5
4
2