የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት፣ ከኢትዮጵያ አቅጣጫ ወደ ሱዳን ግዛት ገብቷል ያለውን ድሮን ዛሬ ጧት መትቶ መጣሉን አስታወቀ፡፡
የሱዳን ጦር ኃይል ድሮኑን መትቶ የጣለው፣ ከኢትዮጵያው ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጋር በሚዋሠነው ብሉ ናይል ግዛት ውስጥ መኾኑን እንደገለጠ የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ኾኖም የሱዳን ጦር ኃይል መትቼ ጣልኩት ባለው ድሮን ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ አንዳልሠጠ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።
የአገሪቱ ጦር ኃይል ከቀናት በፊትም በዚሁ ግዛት ውስጥ ኩርሙክ ከተማ አካባቢ ከኢትዮጵያ በኩል የገባ ድሮን መትቼ ጥያለሁ ማለቱ አይዘነጋም።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ውንጀላዎች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በይፋ ምላሽ አልሠጠም።(ዋዜማ)
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14
3August 27, 2026 2.7K