አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30884 — TG.ME

የምሽቱ ትልቁን ፍልሚያ ጆኒ አሸነፈ

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ሲካሄድ የሰነበተው የኢቲኤፍሲ 2 (ETFC 2) ኮከቦች ምሽት በጉጉት በተጠበቀውና በዋናው የዋንጫ ፍልሚያ (Main Event) በይፋ ፍጻሜ አግኝቷል!

በሚድል ዌይት (Middleweight MMA Bout) ዘርፍ በጆኒ እና በሴዶ መካከል የተደረገው ይህ አስደናቂና አቃጣጣኝ ፍልሚያ የመላው ተመልካች ቀልብ የሳበ ነበር።

በከፍተኛ የኤምኤምኤ (MMA) ቴክኒክ፣ የላቀ ብቃትና ፍጹም የድል ወኔ ተጋጣሚውን ሴዶን ያሸነፈው ጆኒ፡ የምሽቱን ትልቅ ድል በመቀዳጀት አዲሱ የ ETFC 2 ቻምፒዮን (Champion) በመሆን ዘውዱን ደፍቷል!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍17🤣6❤4🤪2🎉1😡1
August 28, 2026 3.1K