የታሪኩ ጋንጋሲ አነጋጋሪ መልእክት
ማደሪያ የሌለው ህዝብ - ሲገፋ የኖረ
እርግጫ ለማየት - ጎዳና አደረ (ታሪኩ ጋንጋሲ)
በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ታፕ ፋይት ቻምፒዮና (ETFC 002፤ Adwa Fight Night) ዋና ፍልሚያ ጆኒ ጁጁትሱ ሰዶን ማሸነፉን ተከተሎ፣ ታዋቂው ድምፃዊ ታሪቁ ጋንክሲ በማህበራዊ ሚዲያው ያስተላለፈው የትችት መልእክት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን በሳበው በዚህ ውድድር ዙሪያ ድምፃዊው «ማደሪያ የሌለው ህዝብ - ሲገፋ የኖረ፣ እርግጫ ለማየት - ጎዳና አደረ» የሚል ግጥማዊ ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን፣ ይኸውም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን የፍትህ ማጣት፣ የጦርነት ስቃይ፣ ተቋማዊ የሌብነትና የዘረፋ ወንጀል እንዲሁም የከፋ የኢኮኖሚ ውደቀት ችላ በማለት ህዝቡ ጥልቅ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ውስጥ እያለ በእንደዚህ አይነት የትግል ትዕይንቶች ላይ ትኩረት ማድረጉን ለመኮነን እንደሆነ ተገልጿል።
ድምፃዊው ይህን ማህበራዊ ተቃርኖ በማንሳት የሰጠው አስተያየት በበርካቶች ዘንድ ድጋፍና የተለያየ ትችት በማስተናገድ በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሰፊ አከራካሪ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

36
12August 28, 2026 2.2K 5