የሟቾች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል
በኔፓልና በቻይና ቲቤት በተከሰተ ከባድ ጎርፍ ከ390 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሲቀጠፍ፥ ከ1ሺ 500 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ሲሉ የአካባቢው ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
አደጋው በሂማሊያ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ ከፍተኛ የጭቃና የድንጋይ ናዳ በመውደቁ የተነሳ ሲሆን፣ በአካባቢው ከተሞችና ሸለቆዎች ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ አስከትሏል።
የነፍስ አድን ሰራተኞች ሰዎችን በህይወት ለማትረፍ መረባረባቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል ተብሏል።
የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቺያንግ በቲቤት የደረሰውን አደጋ በቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል።
የኔፓል ቱሪዝም መምሪያ ትላንት ባወጣው መረጃ፣ ከ34 አገራት የመጡ 668 ቱሪስቶች ከረቡዕ ጠዋት ጀምሮ የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልጿል።
ከእነዚህም መካከል ቢያንስ 177 ከህንድ፣ 90 ከአሜሪካ፣ 34 ከአውስትራሊያ፣ 33 ከብሪታንያ እና 25 ከካናዳ የመጡ ናቸው ብሏል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በኔፓል ከጠፉት መካከል 100 የቻይና ዜጎች እንደሚገኙበት እወቁልኝ ብሏል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13
9
2August 28, 2026 4.6K 5


