አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30920 — TG.ME

የ 46 አመቱ የአንበሳ ባንክ ጥበቃ የ 12 ክፍል ፈተናን 320.25 ዉጤት አመጡ

👉🏼ባንኩ በዉጤቱ ተደስቶ የተለያዩ ስጦታዎችንም አበርክቶላቸዋል


የአንበሳ ባንክ የጥበቃ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ሰይፈ ተስፋዬ ካሕሳይ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማለፊያ ነጥብ ማግኘታቸዉን ዳጉ ጆርናል ከባንኩ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ሰለዋ ወረዳ ደላ ከተማ በሚገኘው የአንበሳ ባንክ ቅርንጫፍ ላለፉት ሰባት አመታት በጥበቃ ስራ እየሰሩ የሚገኙ አቶ ሰይፈ በ46 አመታቸው የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቅያ ፈተና ተፈትነው 320.25 ነጥብ በማምጣት ወደ ዩንቨርስቲ ማለፋቸውን ባንኩ ማሳወቁን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

በዚህም የባንኩ የዳይሬክቶሮች ቦርድ አባላት ፣ ማኔጅመንት እና ሰራተኞች በሙሉ የተሰማቸዉን ደስታ ገልጸዋል።

በዚሁ መሰረት ለአቶ ሰይፈ ተስፋዬ ባንኩ ማበረታቻዎች ለመስጠት ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን አቶ ሰይፈ ተስፋይ ካሕሳይ ወደ ዩንቨርስቲ ለመግባት እና ለመማር የሚያስፈልጋቸው ማንኛውም ወጪ የዩንቨርስቲ ቆይታቸው እስከሚያጠናቅቁ ድረስ ሙሉ ወጪያቸውን ባንኩ እሸፍንላቸዋለሁ ብሏል።

በተጨማሪም አቶ ሰይፈ ወደ ዩንቨርስቲ ከገቡበት ወር ጀምሮ አሁን የሚከፈላቸ ወርሃዊ ደመወዝ ሙሉ በሙሉ በየወሩ ለቤተሰቦቻቸው እንዲከፈል እንደሚደረግም ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

በሌላ በኩል አቶ ሰይፈ ተስፋይ ካሕሳይ የዩንቨርስቲ ትምህርታቸው ካጠናቀቁ በኋላ ባንኩ በተገቢው የስራ ዘርፍ በመመደብ በቋሚነት ቀጥሮ የሚያሰራቸው ይሆናል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤10👍5
August 29, 2026 663 1